ዜናዎች

” ወላይታ ድቻን ከፍ ማድረግ ነው ዘንድሮ የምንፈልገው፤ ያሳደገን ቡድንም ስለሆነ ” -ቸርነት ጉግሳ

የወላይታ ድቻ በጥሩ አቋም ላይ ከሚገኙ ተጨዋቾች አንዱ ቸርነት ጉግሳ ነው። ቸርነት ቡድኑ የዛሬውን ጨዋታ በአቻ ውጤት እንዲወጣ ሁለተኛ ጎል በ83ኛ ደቂቃ አስቆጥሯል።ከጨዋታው በኋላ ቸርነት ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
የዘንድሮው የውድድር ዓመት እንዴት እየሄደ ነው እየሄደ ያለው ?
“የዘንድሮው የውድድር ዓመት አጀማመሬ አሪፍ ነበር መሃል አካባቢ ትንሽ የመቀዛቀዝ ነበር ከጉዳት ጋር ነገር ግ አሁን ወደ ተክክለኛው አቋም እየመየመጣሁ ነው ብዬ አስባለሁ።”
ዛሬ ስላስቆጠረው ጎል ?
” ጎሏን ሳስቆጥራት ፊቴን እንዳዞር ብቻ ነበር የፈቀዱልኝ እኔም ፊቴን እንዳዞርኩ ነበር የመታዋት እግዚአብሔር ፈቅዶ ኳሱ ተሳክቶልኝ ወደ ጎል ገብቷል”
በአንድ ሊግ ውስጥ ከሶስተ ወንድሞች ጋር አብሮ ስለመጫወት : አንተነህ ጉግስ አብሮት ይጫወታል በዚህ ላይ ሃሳቡን ?
” እዎ ! ከወንድም ጋር ስትጫወት በጣም ነው ደስ የሚለው። ኳሶች ሲበላሽብህ ያበረታታሃል፣ ችግርህን ይነግርሃል። በጣም ነው ደስ የሚለው ከወንድም ጋር መጫወት “
የዘንድሮው የውድድር ዓመት እንደቤተሰብ እቅድ አላችሁ ?
” ወላይታ ድቻን ከፍ ማድረግ ነው ዘንድሮ የምንፈልገው፤ ያሳደገን ቡድንም ስለሆነ።
በፋሲል ከነማ ስለሚገኘው ወንድሙ ሽመክት
” አዚህ ደረጃ ለመድረሴ ሽመክት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የእሱን ፈለግ ነው የምከተለው። እሱ ነው የሚያበረታታኝ። እሱ ሲጠነክር እጠነክራለሁ። አሁን እሱም አሪፍ ላይ ነው።
ዛሬ ያስቆጠርከውን ጎል ለሽመክት ይሁንልህ ?
” በፈገግታ አይ ….ጎሉ ለእናት እና አባቴ ይሁንልኝ “