ቶማስ ስምረቱ ➖ወልቂጤ ከተማ
ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ክለቤ ላለመውረድ በሚጫወትበት በራሴ ላይ ጎል በማስቆጠሬ በጣም አዝኛለሁ ፣ለደጋፊዎች ይቅርታ ” – ቶማስ ስምረቱ

ቶማስ ስምረቱ ➖ወልቂጤ ከተማ
ቶማስ ስምረቱ ➖ወልቂጤ ከተማ

 

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ 25ኛ ሳምንት  የወልቂጤ ከተማ እና የሰበታ ከተማ ጨዋታ በሰበታ ከተማ 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል። የጎሏ  መገኘት ደግሞ የሰበታው አጥቂ ኦሰይ ማውሊ የሻገረውን ኳስ የወልቂጤ ከተማው ጠንካራ ተከላካይ ቶማስ ስምረቱ  ተነክታ  ኳሷ ከመረብ ላይ ተዋህዳለች ።
በወልቂጤ ከተማ በኩል የተከላዮ ስፍራ ጠንካራ ደጀንና ረዣዥም ኳሶችን በቀላሉ ወደፊት የሚያሻግረው ቶማስ ስምረቱ  መጥፎ የእግርኳስ አጋጣሚ እንዲሆን አስችሏቸዋል። ኢትዮኪክ ከዋልያዎቹ እና ከወልቂጤ ከተማ ተከላካይ ቶማስ ስምረቱ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል።
ኢትዮኪክ:- የዘንድሮ የውድድር ዓመት ቡድናችሁ ሲጀምር ጥሩ ጅማሮ ነበር ፣ አሁን ላይ ግን በወራጅ ውስጥ ይገኛል ?
ቶማስ :- አዎ ። አሁን ላይ ያለንበት ደረጃ እንደ አደጀማመራችን  የሚገባን ይሄ አለነበረም። ጅማሮ ላይ የነበረን ጥንካሬ ለዋንጫው ከተገመቱት አድርጎንም ነበር። ግን ውጤቱ አሁን ያለንበት ቦታ የሚገባንም አይደለም።
ኢትዮኪክ:- ክለባችሁ በሊጉ የመቆየቱ ዕልወና በቶማስ እንዴት ይገለፃል ?
ቶማስ :- አዎ በቀጣይ አንድ  ጨዋታ እና የሌሎችም ውጤት ይወሰነናል። በርግጥ የመጀመሪያ ዙር የነበረን እና አሁን ያለን ደረጀ በጣም ያሳዝናል። አውነት ለመናገር እንደዚህ ደረጃ እንደርሳለን ብለን አላሰብነውም። እንደ ተጨዋች በጣም ይሰማሻል። ከዚህ በተጨማሪም ሙሉ ለሙሉ አሁንም ዕድላችንን የተሟጠጠም አይደለም።
ኢትዮኪክ:- ወልቂጤ ከተማ በጣም ጥሩ ስብስብ ናችሁ  ላላችሁበት ውጤት ምክንያቱ ምንድነው ?
ቶማስ :- እንደተጨዋች ይሄን እኔም አላውቀውም። ለምን ውጤታማ አልሆናችሁም እኔም አላውቀውም …
ኢትዮ ኪክ :- ከሰበታ ከተማ በነበረው ጨዋታ በራስህ  ላይ ጎል በማስቆጠህ በተፈጠረው ነገር በጣም ያዘንክ ትመስላለህ ?
ቶማስ :- አዎ በጣም ተሰምቶኛለ። በርግጥ እንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎች በኳሰ የሚፈጠሩ ቢሆንም እንደ ተጨዋች በጣም ተሰምቶኛል። በግሌ በተጨዋችነት የተፈጠረው ነገር በጣም አዝኛለሁ።
ኢትዮኪክ: – በራስህ ላይ – ያስቆጠራትን ጎሉን አስበኸው ነበር ?
ቶማስ :- ኸረ በፍጹም ! አላሰብኩትም በወቅቱ በተፈጠረው አጋጣሚ እኔም እራሱ ደንግጫለሁ። እንደዛ ይፈጠራል ብዬ አላሰብኩም። እኔም እራሴ በዚህ ሰአት ክለቤ ላለመውረድ በሚጫወትበት ሰአት በራሴ ላይ በማስቆጠሬ ይሄ ነገር በመፈጠሩ በጣም ደንግጫለሁ ፣ አዝኛለሁም።
ኢትዮኪክ:- ኮንትራትህ ዘንደሮ ያበቃል
ቶማስ :- አይ አይደለም ፤ ከክለቡ ጋር እቆያለሁ
ኢትዮኪክ:- በውጤቱ የወልቂጤ ደጋፊዎች በተመለከተ ምን ትላልሀ 
ቶማስ :- ከእኛ የባሰ የሚጨነቁት ፣ የሚያስብት ደጋፊዎች ናቸው። ማለት ተጨዋቾች ተጫውተው ይወጣላቸዋል። እንደ ደጋፊ ግን በጣም ነው የሚጨነቁት ለክለባቸው ስለሚያስቡ በጣም ይጨነቃሉ። ለደጋፊዎቻችን ይህ ውጤት የሚገባው አይደለም። ለደጋፊዎች ማለት የምፈልገው ይቅርታ ማለት ነው። የሚገባው ደረጃ አይደለም ይሄ አይገባቸውም ብዬ ነው የማስበው።