#ከመነሻው ይሄ ስህተት እንዲከሰት መንገዱን የከፈተው ራሱ ፌዴሬሽኑ መጠየቅ ይኖርበታል!
👇
ከጥር 23 -28/2015 ዓ.ም በአሰላ አረንጓዴው ስቴድዮም እየተካሄደ በሚገኘው ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከእድሜ ተገቢነት ጋር በተያያዘ ከዕድሜ በላይ ሆነው የተገኙ አትሌቶችን በሠነድ እና በአካላዊ ምርመራ መሠረት ከውድድር ውጭ መሆናቸውን የኢትዮዽያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይፋ ማድረጉን ዛሬ አሳውቋል።
ይኸ ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ያለ ምንም ማረጋገጫ ዓመታዊውን ከ20 አመት በታች አገር አቀፍ ውድድር አስጀምሮ በአንፃሩ እኛን ጨምሮ በተለያዩ ሜዲያዎች ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ አትሌቶች መወዳደራቸው አግባብ አለመሆኑ ከተነገረ በኃላ ፌዴሬሽኑ ዛሬ ቁጥራቸው ከ250 በላይ አትሌቶችም ከውድድሩ ውጪ መሆናቸውን አሳውቋል !
ፌዴሬሽኑ እንዳለው ከሆነም ተግባሩን በፈፀሙ ቡድኖች አሰልጣኞች ላይም እርምጃ እንዲወሰድ ለየክልላቸው፣ ከተማ አስተዳደራቸው፣ ክለባቸውና ተቋሞቻቸው ፌዴሬሽኑ ማስጠንቀቂያ አዘል ደብዳቤ እንደሚልክ እና ማጣራቱ እስከ ውድድሩ ማብቂያ ድረስ የሚቀጥል እንደሆነ አስውቋል።
ፌዴሬሽኑ ይሆን ይበል እንጂ ከመነሻው ይሄ ስህተት እንዲከሰት መንገዱን የከፈተው ራሱ የኢትዮጵያ የኢትዮዽያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደሆነ ግልፅ ነው። ፌዴሬሽኑ ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ማጣራት እና መስራት የነበረበትን ስራ አሁን ከሜዲያ ከስፖርት ቤተሰቡ ጩኸት በኃላ መንቀሳቀስ ከተጠያቂነት የሚያስቀረው ተግባር አይሆንም ።
መረጃ
👇
በቴሌግራም :-
https://t.me/Ethio_Kickoff
በኢንስታግራም ገጻችንን :-
https://www.instagram.com/ethio_kick
🔛ድረ ገጻችንን :-