በሊቢያ ሊግ ተሳታፊ ለሆነው አል መዲና ትሪፖሊ እግር ኳስ ክለብ የሚጫወተው ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር ተጫዋች ከንአን ማርከነህ ከክለቡ ጋር ያለውን ውሉን መቅደዱና መለያየቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለኢትዮ ኪክ መረጃውን ጠቁመዋል ።
የከንአን ማርከነህ ክለብ አል መዲ ቱንዚያዊውን አሰልጣኝ አሰናብቶ አዲስ ግብፃዊ አሰልጣኝ መቅጠሩ ተከትሎ አዲሱ አሰልጣኝ ሦስት አፍሪካውያን ተጨዋቾች ወደ ክለቡ ማስፈረማቸው ሲሰማ አዲሱ ግብፃዊ አሰልጣኝ ብዙም ከከንአን ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደሌላቸው ተሰምቷል::
የሊቢያ ሊግ የተጨዋቾች ዝውውር February 17 መዘጋቱን ተከትሎ የከንአን ማርከነህ ቀጣይ ማረፊያ ክለብ ገና የታወቀ ነገር ባይኖርም እዛው በሊቢያ ሊግ ለመቀጠል የሚያስችሉ ዕድሎች እንዳሉት የኢትዮ ኪክ ታማኝ ምንጮች መረጃውን ጠቁመዋል ።
የዋልያዎቹ ተጨዋች የከንአን ማርከነህ ከክለቡ ቆይታው በወዳጅነት እና በሊጉ ጨዋታ ላይ ጎል ማስቆጠሩ ይታወሳል:: በቀጣይ ከንአን ማርከነህ ጋር ተጨማሪ መረጃዎችን እናደርሳለን ::