ዜናዎች

” ከማዳጋስካር ጋር ወሳኝ ጨዋታ ነው : ዘንድሮ ለአፍሪካ ዋንጫ እናልፋለን ብዬ በርግጠኝነት እናገራለሁ ” – ሽመልስ በቀለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ድንቅ የአማካይ ክፍል ተጨዋች እና የዘንድሮው በግብፅ ፕሪምየር ሊግ ከከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች አንዱ በተጨማሪም የየካቲት ወር ምስር ኤል ማካሳ የወሩ ኮከብ ተጫዋች ሽመልስ በቀለ ለኢትዮ ኪክ ዘንድሮ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ቁልፉ በእጃቸው እንደሆነም ይናገራል።
ኢትዮ-ኪክ :- የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ዳግም ለመጫወት የሽመልስ ዝግጅት ?
ሽመልስ :- ይሄ ጨዋታ ለእኛ ትልቅ ነገር ነው። ከማዳጋስካር የምናደርገው የዕረቡ ጨዋታ ለቀጣይ እና የመጨረሻው ጨዋታ ትልቅ ምዕራፍ የሚሆነው። ስለዚህም በአጠቃላይ የቡድኑ አባላት አሁን ላይ ትልቁ ትኩረታችን የመጀመሪያው ጨዋታ ማሰነፍ የሚለው ላይ ነው። ምክንያቱም የዕረቡን ጨዋታ እዚሁ ጨርሰን ማሸነፍ አለብን። ይህንን ከማዳጋስካር ጋር የሚኖረውን ጨዋታ የምናሸንፍ ከሆነ ደግሞ አንፃራዊ በሆነ መልኩ 80% ለአፍሪካ ዋንጫ እንዳለፍን አድርጌ ነው የማስበው።

ኢትዮ-ኪክ :- አሁን ያለው ቡድን ማዳጋስካርን ማሸነፍ እና የአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ተስፋ አለው?

ሽመልስ : – አዎ። ያንን ለማድረግ የሚችል ቡድን ነው። ይህንን የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ቁልፉ በእጃችን ነው። ከማዳጋስካር ጋር ወሳኝ ጨዋታ ነው። ጨዋታውን አሸንፈን ለአፍሪካ ዋንጫ እናልፋለን ብዬ በርግጠኝነት እናገራለሁ።
ኢትዮ-ኪክ :-የአሁኑ የብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ከበፊት ቡድን የተሻለ የሚደርገው ?
ሽመልስ :- ሁሉም ተጨዋቾቹ ጥሩ በቃት ላይ ናቸው። ከውድድርም ስለመጡ ሁሉም የግል ብቃታቸው ጥሩ ነው። በጣም የተሻለ ቡድን ነው። ከበፊቱ የተሻለ ነገር እንሰራለን ብዬ አስባለሁ። የአገሪቱ የሊግ ውድድር በሳምንት ሁለት ጊዜ ከበፊቱ የተለየ ሂደት ላይ ነው። ስለዚህ ከዚህ ውድድር ውስጥ ሲመጡ የተለየ ነው።
ኢትዮ-ኪክ :- በወዳጅነት ጨዋታው ማላዊን ማሸነፋችሁ ቡድኑን ጠንካራ ያስበለዋል ?
ሽመልስ : – ባለፈው ባደረግነው የወጃነት ጨዋታ ላይ የእኛ ቡድን እና ጓደኞቼ ጥሩ በቃት ላይ እንደሆንን በይበልጥ ያሳየበት ነው። የማሊ ቡድን በርግጥ አብዛኞቹ ተጨዋቾች በአገሪቱ የሊግ ውድድር ከሁለት በፊት በመቋረጡ ውድድር ላይ ያልነበሩ ናቸው። የማሊ ቡድን ደካማ መሆን እንዳለ ሆኖ በጨዋታ ላይ ግን የእኛ ሁሉም ተጨዋቾች ትኩረት ሰጥው ነበር ሲጫወቱ የነበረው። በርግጥ በጨዋታው ላይ በቡድናችን ድክመት የታዮበት እና መስተካከል የሚገባቸው ነገሮች ነበሩ። ይሁንና ያንን ክፍተቶች እና መስተካከል የሚችሉ ድክመታችንን በቀሪዎቹ ቀናቶ አሻሽለን ለዕሮብ ከማዳጋስካር ጋር ጨዋታችንን በብቃት ለመወጣት ነው የምናስበው።
ኢትዮ-ኪክ :- የቤትኪንግ በቀጥታ መታየቱ ለአገር ውስጥ ተጨዋቾች የሚሰጠው ጠቀሜታ ?
ሽመልስ :- የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በጣም ትልቅ ነገር ነው። ምክያቱም እዛ ሆኜ እከታተላለሁ። ያ ነገር ደግሞ አሁን እኔ ብቻ ሆኜ የማስብበትን እንዳላብ ያደርገኛል። የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቀጥታ ሽፋን ማግቱ በቀጣይ ለብዙ ተጫዋቾች ውጭ ወጥተው የሚጫወቱበት ዕድል ይከፍታል ብዬ አስባለሁ። በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አሪፍ ተጨዋቾች አሉና ይሄ ደግሞ በመላው ዓለም መታየቱ ለተጨዋቾች ትልቅ ነገር ነው። እናም ተጨዋቾች አሁን ካሉበት ቦታ የተሻለ ቦታ ለማስቀመጥ ይሄ መንገድም ይሆናል ብዬ አስባለሁ።
ኢትዮ-ኪክ :- የዘንደሮው የሽሜ የተለየ አቋምና የሚሰማው ስሜት ?
ሽመልስ :- እኔ አሁን ላይ የሚሰማኝ ስሜት ይህንን የአፍሪካ ዋንጫ ማሳካት እፈልጋለሁ። ለእኔም ሁለተኛ ተሳትፎዬ ይሆናል ። ለዚህም ከምንም በላይ በእግር ኳስ ህይወቴ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ይሆናል ማለት ነው። እናም ከእግዚአብሔር ጋር እግዚአብሔርም ይረዳናል ብዬም አስባለሁ። ከጓደኞቼ ጋር ጥሩ ነገር ለመስራትም አስባለሁ። ዳግም በአፍሪካ ዋንጫ ለማሳለፍ ከጓደኞቼ ጋር ብቁ ነንም ብዬ አስባለሁ። ከምንም በላይ ትልቅ ትኩረት የሰጠሁበት ጨዋታ ነው። እግዚአብሔር ዕድሜ እና ጤንነቱን ለዚህ ጨዋታ ይስጠን ነው የምለው።

One thought on “” ከማዳጋስካር ጋር ወሳኝ ጨዋታ ነው : ዘንድሮ ለአፍሪካ ዋንጫ እናልፋለን ብዬ በርግጠኝነት እናገራለሁ ” – ሽመልስ በቀለ

  1. እኛ ኢትዮጵያዊያን ህልማችን መቼም የኢትዮጵያ ከፍታ ነው የሚናፍቀን በየትኛውም አለም እግዚአብሔር በብርታትና በሀይል ጨዋታውን በድል እንድናጠናቅቅ ይርዳን እናት ኢትዮጵያ ሁሌም ከፍ ብለሽ ታይ ለነጌ ጨዋታ ደግሞ ደጋፊም ሆነ ተጨዋች የበኩሉን ድርሻ ለመወጣትና ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆን አለበት ሁሌም ድልና ድምቀት ለብሔራዊ ቡድናችን

Comments are closed.