ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” እውነት ለመናገር ዛሬ ፍፁም ቅጣት ምት አገባለሁ እያልኩ መልበመሻ ክፍል እያወራው ነበር ” – ሐይደር ሸረፋ

ሐይደር ሸረፋ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታ ሐይደር ሸረፋ ባስቆጠረው ሶስት ጎሎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልቂጤ ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል።  የውድድር ዓመቱ የአማካይ ስፍራውና የመጀመርያው  ሀትሪክ  የሰራው ሐይደር ሸረፋ ከጨዋታው በኋላ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።

በቅድሚያ ሶስት ጎሎች በማስቆጠርህ እንኳን ደስ አለህ ?
” አመሠግናለሁ “
በዛሬው ጨዋታ ወደ ሜዳ ሲገባ ጎሎች አስቆጥራለው ብሎ ስለማሰቡ ?
” ዛሬ እውነት ለመናገር ጎል አገባለሁ የሚል ስሜት ነበረኝ። ግን ሀትሪክ አልነበረም። አንድ ጎል ምናምን ነበር ያሰብኩት”
ካስቆጠራቸው ጎሎች ለእሱ ውበት የነበረው ?
“የመጀመሪያው ጎል የሚያምር ጎል ይመስለኛል”
ፍፁም ቅጣት ምቱ ሃትሪክ ለመስራት ወይስ እስተዋለሁ የሚል ስሜት ነበረው?
” እውነት ለመናገር ዛሬ ስንገባ የቡድኑ ፍፁም ቅጣት ምት የሚመታው ሳልሀዲን ነው፣ ግን ሳልሀዲን ባለመኖሩ አገባዋለው እያልኩ መልመሻ ክፍል አያወራው ነበር እና ሁለት ጎል በማግባቴ ፍፁም ቅጣት ምት ልመታ ችያለሁ”
ለተኛ ሆኖ ለመጨረስ የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ታስፋ ስለማድረጉ ?
” ኳስ ነው ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም ሲጫወቱ ብናይ ይሻላል”
የውድድር ዘመኑን እንዴት ነበረ፣ ባሰበከው መንገድ ሄዷል ወይስ ?
“በተለያዩ ችግሮች ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚጠበቅበትን አልሄደም። ለእኛ አስቸጋሪ ጊዜ ነበረ በአጠቃላይ ከውጤት አንፃር እንደዛ ነው የምገልፀው”
የዛሬው የጨዋታ ቀን በተመለከተ
” በጣም ጥሩ ቀን ነበረ ፣ በህይወት ታሪኬ ሀትሪክ ሰርቼ አላውቅም”
የዛሬውን ጎሎች መታሰቢያነቱ ?
‘ (በፈገግታ) ለእናቴ “