ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“እስካሁን አዲስ ነገር ልንባባል የምንችልባቸው አንዳችም ነገሮች የሉም ፣ ሁሉም ነገር እንደዛው እየሄደ ያለው” -አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ

የሀዲያ ሆሳዕናን ስፖርት ክለብ ዘንድሮ ጠንካራ ቡድን ሆኖ ለሶስተኛ ደረጃ እንዲያጠናቅቅ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ትልቁን ስራ ተወጥተዋል።
በአንፃሩ በአሁኑ ሰዓት አሰልጣኙ የስራቸውን እና የቡድናቸውን የመጨረሻ ውጤት እንዳይመለከቱ የስራ ነፃነታቸው ተገፎ ከስፓርቱ ጋር እውቀት በሌላቸው ግለሰቦች ጫና እየደረሰባቸው ይገኛል።
ከዚህ ሌላም በአሰልጣኝ አሸናፊ ላይ የማስፈራሪያ እና ዛቻ ጫና እያስተናገዱም ይገኛል። የሀዲያ ሆሳዕና ክለብ ዋና አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሰሞኑ ችግር አሁንም ምላሽ አላገኘም። አሰልጣኝ አሸናፊም ደብዳቤ አስገብተው ምላሽ እየጠበቁ ይገኛል። ኢትዮኪክ ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር ቆይታ አድርገናል እንሆ :-
ኢትዮኪክ:- የሀዲያ ሆሳዕና ክለብ ሰሞኑን ጫና ውስጥ ይገኛል ፣ እርሶ የስራ ነፃነቶት ተገፎ እንደነበር ይታወቃል- አሁንስ ምን አዲስ ነገር አለ?
አሰልጣኝ አሸናፊ: – እስካሁን እንግዲህ ከሰማሽው ውጪ የተለየ ነበር የለም ። እስካሁን ይሄ ነው አዲስ ነገር ልንባባል የምንችልባቸው አንዳችም ነገሮች የሉም ። ሁሉም ነገር እንደዛው ባለበት እየሄደ ያለው። የተለወጠ ምንም ነገር የለም።
ኢትዮኪክ:- ከቡድኑ ጋር ልምምዶች እየሰሩ ግን እንደሆነ ይታያል ?
አሰልጣኝ አሸናፊ: – አዎ ከቡድኑ ጋር ልምምዶች እየሰራን ነው። በሌላ በኩል ግን ምንም የተለየ ነገር የለም።
ኢትዮኪክ:- በዚህ መልኩ ምንም የተለየ ነገር ከሌለ በቀጣይ ጨዋታስ ቡድኑን እንዴት ነው የሚሆነው?
አሰልጣኝ አሸናፊ: – ገና እንግዴ የክለቡን ውሳኔ እየጠበቅን ነው። ምን ሊከሰት እንደሚችል አላወቅንም። ከዚሁ ጋር አሁን በዚህ ሰአት ምንም አይነት መግለጫ መስጠት አልችልም ። ዝም ብሎ ከማየት ውጪ
ኢትዮኪክ:- ስለዚህ ቀጣይ ጨዋታውን በተመልካች ቦታ ሆነው ነው የሚከታተሉት ?
አሰልጣኝ አሸናፊ: – አዎ ። እንግዲህ የሚመጣውን ነገር ዝም ብዬ ማየት ነው ።
ኢትዮኪክ:- ከቀጣይ ጨዋታ በፊት አዲስ ነገር ሊኖር ይችላል በኩለቡ በኩል ብለው ይጠብቃሉ ?
አሰልጣኝ አሸናፊ: – በእውነቱ የሚታወቅ ነገር የለም።
ኢትዮኪክ:- ከዚሁ ጋር ተጨዋቾች የወሰኑት ውሳኔ ትክክል ነው ይላሉ?
አሰልጣኝ አሸናፊ: – ተጨዋቾች የጠየቁት እኮ ከክለቡ ጋር የተስማሙትን ነው። የተለየ ነገር አይደለም። የመብት ጉዳይ ነው የጠየቁት ። ክለቡ ደግሞ እሰጣችኋለሁ ብሎ የተዋዋለው ነገር አለ ። ስለዚህ ያነንን መፈጸም ያለመፈፀም የመብት ጉዳይ ነው እንጂ የጠየቁት የተለየ ነገር አይደለም። ከዛ ደግሞ ተጨዋቾች ያለመኖር እና በጎዶሎ ተጨዋቾች መጫወት የሚፈጥረውን ክፍተት እንደታየው ነው። 15 የሚያህል ጠንካራ ተጨዋቾችን ማጣት ከባድ በጣም ነው። ስለዚህ ይሄ ነው ያለው ነገር።
ኢትዮኪክ:- የተቀጣው ተጨዋች አሁንም በቀጣይ ጨዋታ ይኖራል ?
አሰልጣኝ አሸናፊ: -እሱንም ክለቡ ነው የሚወስነው።
ኢትዮኪክ:- እርሶ ደብዳቤ አስገብተዋል ስለሚባለው ነገር ?
አሰልጣኝ አሸናፊ: – አዎ። ሌላ ነገር አይደለም ።ደብዳቤ አስገብቻለሁ – ይኸም ደብዳቤ የስራ ጣልቃ ገብነት አይኑር በሚል ስለተከሰተው ነገር ሲሆን ክለቡ በዚህ ላይ የሚሰጠውን ምላሽ እየጠበኩ ነው።
ኢትዮኪክ:- ከክለቡ ጋር።ያሎት የስራ የውል ዘመኖ መቼ ይጠናቀቃል ?
አሰልጣኝ አሸናፊ: – እንግዴ አሁን ውል አለኝ እሰከ ሰኔ 30 ድረስ። ስለዚህ የሚሉትን እጠብቃለሁ ።
ኢትዮኪክ:- ደጋፊዎች ተቃውሞ እያሰሙ ነው ፣ በዚህ ላይ የሚሉኝ ካለ ?
አሰልጣኝ አሸናፊ: – የደጋፊውን ነገር ምንም የሰማሁት ነገር የለም። ማንኛውም ደጋፊ መቃወምና መደገፍ መብቱ የተጠበቀ ነው። በዚህ ዙሪያ ምንም ዓይነት መረጃ የለኝም።
ኢትዮኪክ:- አሰልጣኝ አሸናፊ ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሠግናለሁ ።
አሰልጣኝ አሸናፊ: – እግዚአብሔር ይስጥልኝ። እኔም አመሠግናለሁ

2 thoughts on ““እስካሁን አዲስ ነገር ልንባባል የምንችልባቸው አንዳችም ነገሮች የሉም ፣ ሁሉም ነገር እንደዛው እየሄደ ያለው” -አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ

  1. Asalixagni ashanaf bakalani inwodaleni inga ye hadiya hosana dagafiwochi machemi anasazi tilik asalixagni mahoninihin awukallo inkabiraleni bamakaxali betachin na clubachin yetafaxarawuni chigir ashanafini ayimalakatimi yemimalakataw ikali lay irmija insidaleni

Comments are closed.