ዜናዎች

-ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ወሳኙን የደረጃ ጨዋታ በዋና ዳኛነት ይመሩታል !

በዓለም አቀፍ እና በአህጉር አቀፍ ውድድሮች ላይ በዋና ዳኝነት እና በረዳት ዳኝነት በብቃት በመወጣት የሚታወቁት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ነገም በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ተጠባቂውን የደረጃ ጨዋታ በዋና ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል ።
በቶኪዮ ኦሎምፒክ ሰሞኑን በዋና እና ረዳት ዳኝነት የመሩት ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ዓርብ የኦሎምፒክ አዘጋጇ ጃፓን ከ ሜክሲኮ ለሶስተኝነት (ለነሀስ ሜዳሊያ) የሚያደርጉትን ታላቅ ፍልሚያ በዋና ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።  የቶኪዮ ኦሊምፒክ የነሀስ ሜዳሊያ ጨዋታ ነገ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር 8 :00 ሰአት የሚካሄድ ይሆናል።

One thought on “-ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ወሳኙን የደረጃ ጨዋታ በዋና ዳኛነት ይመሩታል !

Comments are closed.