ቀጥታ ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀጥታ ስርጭት ከነገ ጀምሮ ይቀጥላል !

👇
የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስት ሳምንታት ውድድር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዶ በብሔራዊ ቡድን እና የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር ምክንያት መቋረጡ ይታወቃል። ከ6ተኛው ሳምንት ጀምሮ ያሉ የሊጉ ጨዋታዎች ከነገ ህዳር 20/2016 ጀምሮ በወጣው መርሃ ግብር መሰረት መካሄዱ የሚቀጥል ሲሆን የሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭተም ይጀምራል። በስምምነቱ መሰረት በ2016 ዓ.ም በቀጥታ ስርጭት ከሚተላለፉ አንድ መቶ ሰማንያ(180) ጨዋታዎች ውስጥ ስምንት ጨዋታዎች ሽፋን በማግኘታቸው በቀጣይ ከሚካሄዱ ጨዋታዎች ውስጥ አንድ መቶ ሰባ ሁለቱ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ይኖራቸዋል። በተጨማሪም የAi(Artificial intelligence) ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከስምምነቱ ውጭ ያሉ ጨዋታዎችን ለማስተላለፍ አክሲዬን ማህበሩ ከሱፐር ስፖርት ጋር በመነጋገር ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ