ዜናዎች

ኢትዮጵያ የሴካፋ ውድድር ሻምፒዮን በመሆን ዋንጫውን አነሳች!

በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የነበረውን የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ሀገራት ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሻምፒዮናነት አጠናቃለች።
በስድስት ሀገራት መካከል በዙር ሲካሄድ በቆየው ጨዋታ ኢትዮጵያ አምስቱንም ጨዋታ በማሸነፍ የሻምፒዮናነት ክብሩን አንስታለች። 
በተለይም ዛሬ ለፍፃሜ  ከዮጋንዳ ጋር በተደረገው ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ  በ5ኛው ደቂቃ ላይ ግብ ጠባቂ  እየሩሳሌም ጥፋት ፈፅማለች በሚል በቀይ ካርድ ከሜዳ በመውጧቷ ታዳጊዎቹ   በ10 ተጨዋቾች   በ2 ለ0 እየተመሩ የመጀመረያ  45 ጨዋታውን ያጠናቀቁት።
ይሁንና በሁለተኛው አጋማሽ   ጨዋታው ተለውጦ  አስገራሚ ውጤት ተመዝግበዋል። በውድድሩ ኢትዮጵያ ሻምፒዮን በመሆን የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ስትሆን ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ በቅደም ተከተሉ መሠረት የብርና የንሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።