የዘንድሮ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሐምሌ 1/2013 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቀድሞ ቢያሳውቅም ትላንት በተረጋገጠው መረጃ በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ እና በኮንፌዴሬሽን ካፕ ለሚሳተፉ ክለቦች የዝውውር መሥኮቱ ከመከፈቱ በፊት ቀደም ብሎ ማካሄድ እንደሚችሉ መፈቀዱ ተዘግቧል።
በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ከነገ ጀምሮ አዳዲስ ተጨዋቾች የሚያስፈርም እና ውል የጨረሱትንም ተጨዋቾች ውላቻውን የማደስ ሂደቶች እንደሚጀምር ለጉዳዩ ቅርበት ካለቸው ምንጮች የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
እንደሚታወሰው በአፍሪካ ኮንፌዴሽን የሚሳተፈው የኢትዮዽያ ቡና ክለብ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታን ከዻግሜ 5 – መስከረም 2 ባሉት ጊዜ በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ያደርጋል። የመልሱን ጨዋታ ደግሞ ከሳምንት በኋላ የሚያደርግም ይሆናል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአፍሪካ መድረክ ለሚወክሉት ፋሲል ከነማ ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ንግድ ባንክ ( ሴቶች )ክለቦች አስቀድመው ለዝግጅታቸው እንዲረዳቸው የተጨዋቾች የዝውውር ሂደታቸውን ከሐምሌ 1 በፊት በመፈቀዱ ክለቦቹ የዝውውር ሂደታቸውን ከ ነገ ጀምሮ እንደሚጀምሩም ተሰምቷል።
በጣም ቆንጆ መረጃ ነው በተቻለን መጠን ክለባችንን መታወቂያችንን በማደስ ማሊያ በመግዛት አጋራችንን ከጎኑ በመሆን እንደግፋለን ። ሌላው 2013 ዓመታዊ የቤተሰብ ሩጫ የለም ካለ ለደጋፊው ከወዲው እንዲመዘገብ መረጃ ስጡት
Really I am very interested by kick off information.