በፈረንሳይ ሌቪን በተደረገው የ2021 የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል።በሴቶች የ1500ሜትር የአምናው የሌቫን አሸናፊ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ዘንድሮ በርቀቱ 3: 53.09 ሪከርዱን ጭምር በመስበር አሸናፊ ሆናለች። ከቀናት በፊት የአለም አትሌቲክ ፌዴሬሽን ባሳወቀው መሠረት ያለፈው ከ20 አመት በታች በሌቫን ያሸነፈቸው የ1500ሜትር ውድድር አዲስ የአለም ሪከርድ ሆኖ እንዲመዘገብ የተደረገላት አትሌት ለምለም ሃይሉ በምሽቱ ውድደር የ3000 ሜትር ርቀቱን ታላቅ ግምት የተሰጣትን ሆላንዳዊት ሲፋን ሀሳን በመቅደም በ8:32,55 ሰአት አሸናፊ ሆናለች።በተመሣሣይ ከቀናት በፊት ድል ቀንቷት የነበረቸው ኢትዮጵያዊቷ ሀብታም አለሙ በሴቶች 800 ሜትር በሁለተኛነት አጠናቃለች። በወንድች የ3000 ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያለውን ድል ተቆጣጥረው አሸንፈዋል። በ3000 ሜትር መሰናክል ሯጭነቱ የሚታወቀው አትሌት ጌትነት ዋለ ቀዳሚ ሲሆን ከቀናት በፊት ድል ቀንቶት የነበረው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በሁለተኝነት አትሌት ለሜቻ ግርማ እና አትሌት በሪሁ አረጋዊ ሶስተኛ እና በአራተንነት ሆነው ድሉን አድምቀዋል።