አፍሪካ ዜናዎች

ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ታላቁን ፍልሚያ ይመሩታል !

የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከሦስት ወራት ቆይታ በኃላ በቀጣይ ሳምንት በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ሲቀጥል ኢትዮጵያዊያን አርቢትሮች ታላቁን ጨዋታዎችን እንዲመሩም መመረጣቸው ይታወሳል።
ከዚህም መሃል በቀጣይ ሳምንት ሐሙስ የደቡብ አፍሪካዎቹ ባፋና ባፋና ከጋናዎቹ ጥቋቁር ክዋክብት ጋር በጆሀንስበርግ በኤፍኤንቢ ስታዲየም የሚያደርጉትን ወሳኝ ጨዋታ ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ይመሩታል።
ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ ሲመራ በረዳትነት ደግሞ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ክንዴ ሙሴ እና ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ተመስገን ሳሙኤል ፣ የጨዋታው አራተኛ ዳኛ ደግሞ ብሩክ የማነ ብርሀን ሲሆን የጨዋታው ኮሚሽነር ሞሃው ጆን ከሌሴቶ መሆናቸው ተገልጿል፡፡