አትሌቲክስ ዜናዎች

ኢትዮጵያዊያን የሚሳተፉበት የቶኪዮ ኦሎምፒክ ታላቅ ፈተና ውስጥ ይገኛል !

በጃፓን በ2020 ይካሄዳል ተብሎ በኮሮና ምክንያት ለዘንድሮ የተራዘመው የቶኪዮ ኦሎፒክ አሁን ሊጀመር ቀኖቶች ሲቀሩት ዳግም ጭንቀት ውስጥ ይገኛል።
በቶኪዮ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመጣው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የጃፓን መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዛሬ ካወጀች በኋላ ከሁለት ሳምንት በኃላ በሚጀመረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ያለ ተመልካች በዝግ ስታዲየም እንዲሆን ተወስኗል።
ሐምሌ 17 የሚጀምረው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓትም ያለተመልካች በተዘጉ በሮች የሚካሄድ ሲሆን ይኸው ያለተመልካች የሚደረግ የመጀመሪያው የኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ይሆናል።
በውድድሩ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን  ለቶኪዮ 2020 (2021) ኦሊምፒክ  የበለጠ ውጤታማ  ለመሆን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቡድኑን መልምሎ ከህዳር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሆቴል በማስገባት ላለፉት 8 ወራት ጠንካራ ልምምድ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ቡድኑ ወደ ጃፓን ለመጓዝ ዝግጅቱን አጠናቆ ቀናቶች እየጠበቀ ይገኛል።