አትሌቲክስ ዜናዎች

– ኢትዮጵያዊው ሰለሞን ቱፋ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ ዲፕሎማ አስገኘ!

ሰለሞን ቱፋ

በወርልድ ቴኳንዶ ድንቅ ብቃትን በማሳየት ለኦሎምፒክ ውድድሩ ኢትዮጵያን በመወከል ወደ ጃፓን ያቀናው ወጣት ሰለሞን ቱፋ በኢትዮዽያ የኦሎምፒክ ታሪክ በ7ተኛ ደረጃ በመጨረስ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል። ሰለሞን ቱፋ ደም ደምሴ በውድድሩ ዲፕሎማ በማግኘት አዲስ ታሪክ ያስመዘገበ ቀዳሚ ሆኗል ።

ወጣት ሰለሞን ቱፋ የመጀመሪያ ዙር ግጥሚያውን በ58 ኪ/ሎ ግራም ከጃፓኑ ሱዚኪ ሰርጂዮ ጋር ተጋጠመው በጥሩ የአጨዋወት ስልት ሶሎሞን ፍልሚያውን በበላይነት ተቆጣጥሮ ማሸነፉ አይዘነጋም።  ሰለሞን ቱፋ በኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ታሪክ በ ወርልድ ቴኮንዶ ለመጀመርያ ጊዜ ያገኘውን የ7ኛ ደረጃ በተመለከተ በሶሻል ሚዲያው ደስታውን “እግዚአብሔር ይመስገን ” በማለት ገልጿል።
የሰለሞን ቱፋ – ዲፕሎማ