ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ኢትዮዽያዊው ዛሬም ጎል አሰቆጥሮ በግብፅ ሊግ መሪነቱን አጠናክሯል !

በግብፅ ፕሪምየር ሊግ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ለቡድኑ ወሳኝ እና ብቸኛ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑን አሸናፊ ያደረገው ኢትዮዽያዊው አማካይ ሽመልስ በቀለ ዛሬም ጎል በማሰቆጥር ቡድኑ ምስር ኤል ማካሳ ከታላቁ ዛማሊክ ቀጥሎ በሁለተኝነት ሊጉን እንዲከተል የበኩሉን አድርጓል። በ14ኛ ሳምንት የዛሬው የግብፅ ፕሪምየር ሊግ የሽመልስ ምስር ኤል ማካሳ ተጋጣሚውን ዋዲ ዳግልን በ3 ለ1 እንዲያሸንፍ ኢትዮዽያዊው ሽመልስ በቀለ በ23ኛው ደቂቃ የመጀመሪያውን ጎል ካስቆጠረ በኃላ ቀሪዎቹን ሁለት ጎሎች አመቻችቶም የሰጠው ኢትዮዽያዊ ሽመልስ በቀለ ነበር። ጎሎቹን ማዳጋስካራዊው ፖውሊን ቫዋቩ በ86ኛው እንዲሁም ግብፃዊው ቤሴም ሞርሲ በ87ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል። ለዋዲ ዳግል ብቸኛውን ጎል ጨዋታው ሊጠናቀቅ በጭማሪ ሰአት ሳላህ አሚን አስቆጥሮ የሽመልስ ቡድን 3 ለ1 አሸንፏል።የዛሬው ጨዋታ ምርጥ እንቅስቃሴ ያደረገውና የጨዋታው ምርጥ ሽልማት ያገኘው ኢትዮጵያዊው አማካይ ሽመልስ በቀለ በ6 ጎሎች በግብፅ የከፍተኛ ጎል አስቆጣዎች ደረጃ ከመሪው በአንድ ጎል ብቻ ተበልጦ በሁለተኝነት እየተከተለ ይገኛል።