ዜናዎች

-ኢትዮዽያዊው አማካይ ሽመልስ በግብፅ ቆይታው የጎል ሪከርዱን አሻሻለ ! – የሱዳን የጎል ሪከርዱ እስካሁን አልተነካም!

በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ዘንድሮ ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ላይ የሚገኘው ኢትዮዽያዊው ሽመልስ በቀለ በዚህም ሳምንት የተለየ የሆነውን ጎል አስቆጥሯል። በግብፅ ፕሪምየር ሊግ ከከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች አንዱ የሆነው የአማካይ ስፍራው ሽመልስ በቀለ በትላንት ምሽቱ ጨዋታ ክለቡ ምስር ለል መቃሳ በአል ሞካውሎን 3 ለ 2 ሽንፈን ቢያስተናግድም ሽመልስ በግብፅ ሊግ ቆይታው ያስቆጠረውን የጎል መጠን አሻሽሏል።
ኢትዮጵያዊው አማካይ ሽመልስ በግብፅ ሊግ በ 2018/2019 የሊጉ ጨዋታዎች ያስቆጠረውች የ10 ጎሎች ሪከርድ ትላንት ምሽት ወደ 11 ከፍ በማድረግ የግሉን ሪከርዱን ማሻሻል ችሏል።
እንደሚታወሰው ሽመልስ በቀለ እ.ኤ.አ 2014 በሱዳን ፕሪሚየር ሊግ በአል-ሜሪክ የአጭር ጊዜ ቆይታው ለክለቡ አል-ሜሪክ በአንድ ጨዋታ 5 ግቦችን በማስቆጠር እ.ኤ.አ. ከ 1996 በኃላ ሽመልስ በቀለ ሪከርዱን በስሙም ጨብጦም ይገኛል ።