የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፀሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 19 /2013 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ለቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ የማራቶን አትሌቶች በትሪያል መምረጥ አስፈላጊ ነው በሚል ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። በውሳኔው መሠረት ነገ ቅዳሜ 23/ 2013 ጠዋት 12 :00 ለቶኪዮ የአትሌቶች ምርጫ ለማካሄድ ትሪያል ውድድር በሰበታ ከተማ ለማካሄድ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በወንዶች አትሌት ቀነኒሳ ጨምሮ 12 አትሌቶችን እንዲሁም በሴቶች 8 አትሌቶች ቢያሳውቁም የአለም ሁለተኛው ፈጣን የማራቶን አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በደብዳቤ ራሱን ከውድድሩ በማግለል አሁንም ድረስ እንደፀና ይገኛል።
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮዽያ የኦሎምፒክ ማራቶን ቡድን የምርጫ ሂደቱን በመቃወም በነገው ቅዳሜ ትሪያል ውድድር እንደማይካፈል በትዊተሩ ላይ በአማርኛ በፃፈው ደብዳቤ ቢያሳውቅም አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከውድድሩ ለመውጣት ዋነኛው ምክንያት ግን ከፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ጋር የጀመሩት አዲስ አለመግባባቶች ስር መስደዳቸው ተሰምቷል ።
አትሌት ቀነኒሳ ለኢትዮጵያ አትሌትክስ ፊዴሬሽን ያቀረበው የቅሬታ ደብዳቤ
“ከላይ በጉዳዩ ለመግለፅ እንደሞከርኩት እኔ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከዚህ ቀደም ለረጅም ጊዚያት በትራክ ፣በክሮሰ ካንትሪ እንዲሁም በሌሎች ውድድሮች የሃገሬን ሰም ሳሰጠራና ሰንደቀላማዋን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ የበኩሌን ሳደርግ የነበርሁ መሆኒን የሃገሬ ህዝብም ሆነ መንግሰት ህያው ምሰከር ነው ፡ ፡
ነገር ግን ከዛሬ አምስት አመት በፊት በብራዚል ዋና ከተማ ሪዬ ዴጀኒሮ የአለም ኦሎምፒክ ውድድር ሀገሬን በማራቶን ውድድር ወክዬ እንዳልሳተፍ በአትሌት ምርጫ ላይ እንዳልካተትና ከውድድሩ እንዲቀር የተደረገ ሲሆን ባለፈው አመት ሲካሄድ በነበርው የጃፓኑ ቶኪዮ የአለም የኦሎምፒክ ውድድር በማራቶን የውድድር ዘርፍ በአትሌትክስ ፊድርሽን ህግ መሰረት ጥሩ ሰዓት ሰለነበርኝ በወቅቱ በምርጫ ውስጥ በመካተት በልምምድ ላይ የነበርኩ ና በኮሮና ቫይረስ በሽታ መስፋፋት ምክንያት ውድድር ለአንድ አመት የተራዘመና ከጥቂት ወራት በኃላ የሚደርግ ሲሆን ቀደም ሲል እንደሚደረገው ጥሩ ሰዓት በኢንተርናሽናል ውድድር ያስመዘገቡ አትሌት በማራቶን ውድድር ሃገሩን በመወከል ይመረጥ የነበርው ህግ በማስቀረት በሃገር ውስጥ የማራቶን ማጣሪያ ውድድር በማድረግ የማራቶን አትሌት ለመምረጥ አዲስ ህግ ፌዴሬሽኑ ያወጣ ሲሆን ይህንን የማጣሪያ ውድድር በብቃት ማነስ ሳይሆን ወቅቱን ያልጠበቀና የውድድር ጊዜውም በጣም የቅርብና አትሌት ላያ ጉዳት ሰለሚሰከትል ያላመንኩበት በመሆኑ በሃግር ውስጥ የተዘጋጀውን ውድድር የማልሳተፍ መሆኔ ታውቆ በቀጥታ ሃገሬን በመወከል ለውድድሩ እንዲመርጥ እየጠቁኝ በምርጫው የማልሳተፍ ከሆነ ፌዴሬሽኑ ሃገርን በመወከል በሚደረጉ ውድድሮች ላይ የማይሳተኝ መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ እንዲሰጠኝና እኔም ሌላ አማራጭ እንዲፈልግ እንዲደረግ እየጠቁኝ ነገር ግን ሃገሬ በምትፈልገኝ ማንኛውም ውድድር ላይ መሳተፍ ከምንግዜውም በላያ በሙሉ ጤንነትና ብቃት ላይ የሚገኝ መሆኔን እየገለፀኩኝ ይህንንም ብቃቴን ወደፊት በሚደረጉ ውድድሮች ላይ የማሳይ መሆኔን እገልፃለሁኝ “
ከሰላምታ ጋር
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
ማንኛውም ሰው በህግ መገዛት አለበት አንተ እንደውም ለሌላው አትሌት አርአያ መሆን ሲገባህ በሀገር ውስጥ ማጣሪያ አልሳተፍም ማለትህ ሀገርንና ህዝብን መናቅ ይመስላል ፌዴሬሽኑም እንደነዚህ ያሉ አትሌቶች ላይ ቆንጠጥ ያለ እርምጃ መውሰድ አለበት የሰበታን ህዝብም ይቅርታ መጠየቅ አለበት።
Very nice