አትሌቲክስ አፍሪካ ዜናዎች

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከ Nike ወደ ቻይናው ታላቅ ኩባንያ አንታ ስፖንሰሩ ዞሯል!

 

◼🔘 ኩባንያው የረጅም ርቀት ሯጮች ማሰልጠኛ በአፍሪካ እንደሚገነባ ይፋም አድርጓል!
👇
በ5000 ሜትር እና በ10,000 ሜትሮች ውድድሮች የአለም ክብረ ወሰን እና የኦሎምፒክ ክብረ ወሰን ባለቤትና የረጅም ርቀት ሯጩ አሁን ላይ ከዓለማችን ሦስት ፈጣን የማራቶን ሰዓት ካላቸው አንዱ የሆነው ኡትዮዽያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከስፖንሰሩ ከNike ኩባንያ ጋር ያለውን ውል ተቋጭቶ ከቻይናው ኩባኒያ አንታ ጋር መስማማቱን ተሰምቷል።
እ.ኤ.አ በ2008 ኦሊምፒክ በሁለቱም የ5000ሜ እና የ10,000 ሜትር ውድድሮች የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት እና በ2004 ኦሎምፒክ በ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ፣ በ5000 ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊው  ቀነኒሳ የቻይና ትልቁ የሀገር ውስጥ የስፖርት ምርቶች ኩባንያ  አንታ ጋር ተስማምቷል ።
ኩባንያው ይፋ ባደረገው መረጃ አንታ የረጅም ርቀት ሯጮች ማሰልጠኛ በአፍሪካ እንደሚገነባ ዛሬ ይፋም አድርጓል።
በተያያዘ መረጃ በፈረንጆቹ December 3 በሚካሄደው የቫሌኒሺያ ማራቶን ላይ አትሌት ቀነኒሳ እንደሚሳተፍ ታውቋል። ቀነኒሳ የየፓሪስ ማራቶን አቅሙን ለመለካት በቫሌንሽያ ማራቶን እና በቀጣይ ውድድሮች የሚወዳደር ይሆናል ተብሏል።