አትሌቲክስ ዜናዎች

አትሌት ሀብታም በ800 ሜትር የዲፕሎማ ተሸላሚ ሆናለች !

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 800 ሜትር ለፍፃሜው የበቃችው አትሌት ሀብታም አለሙ ፍፃሜውን በ 1:57.56 በስድስተኛ ደረጃ  ጨርሳለች ። አትሌት ሀብታም የአመቱን ምርጥ ሰዓቷን ማስመዝገብም ችላለች። ርቀቱን በትውልድ ሱዳናዊት በዜግነት አሜሪካዊት የሆነችው የ19 ዓመቷ አቲንግ ሙ 1:55 .21 በሆነ  ምርጥ  ሰዓት አሻሽላ በቀዳሚነት አሸንፋለች።  ሀብታም አለሙ በ800 ሜትር ያሳየችው ጥረት በርቺ ልትባል ይገባል። አትሌት ሀብታም 6ኛ በመውጣቷ የዲፕሎማ ተሸላሚ ሆናለች፡፡