ዜናዎች

“አቡበከር ናስር የት እንዳለ አላውቅም። ለሁለት ሳምንታት አላየሁትም የልምምድ ቦታ ላይ መገኘት አቁሟል”አሰልጣኝ ጋቪን ሀንት

 

ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር የደቡብ አፍሪካውን ክለብ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ከወራቶችበፊት መቀላቀሉን ይታወሳል።

ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ አቡበከር ናስርን ለአንድ የውድድር አመት ካስፈረመ ከወራቶች ቆይታ በኃላ የሱፐር ስፖርት ዩናይትድ አሰልጣኝ ጋቪን ሀንት አቡበከር ናስር የት እንዳለ አላውቅም በማለት በይፋ ተናግረዋል::

አሰልጣኝ ጋቪን ሀንት ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ አርብ ዕለት በፖሎክዋን ሲቲ ከተሸነፈ በኋላ ለ KickOff.com እንደተናገሩት አቡበከር ናስር “የት እንዳለ አላውቅም። ለሁለት ሳምንታት አላየሁትም የልምምድ ቦታ ላይ መገኘት አቁሟል” ሲል ተናግሯል:: አሰልጣኝ ጋቪን ሀንት ጨምሮም ተጨዋቹ ክለቡን በተቀላቀለባቸው አራት ወራት ውስጥ ያለፈቃድ ጥሎ እየጠፋ በተደጋጋሚ እንዳስቸገራቸውም ገልፀዋል፡፡

አቡበከር በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።በአንፃሩ ተጨዋቹ ሱፐርስፖርት የመልቀቅ ሙከራ ወይም የአካል ብቃት ጉዳይ ወይም የግል ችግር  እንደሚሆን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *