ዜናዎች

አሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን

“የዲ.ኤስ ቲቪ ህይወት ነበርኩ: ምን ያደርጋል ‘አትሩጥ አንጋጠህ’ ይላሉ እናቶች ሲተርቱ : የኢትዮጵያ እግርኳስ እንደዛ ነው ” – አሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የድሬደዋ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን በሱፐር ስፖርት ተወዳጅ እንደነበሩ ይታወሳል። አሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን ከክለቡ በስምምነት መሰናበታቸውን መረጃዎች ቢወጡም ጉዳዪን አሰልጣኙ የሰሙት በማህበራዊ ሜዲያ እንደሆነ ይናገራሉ። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከኢትዮ ኪክ አጭር ቆይታ አድርገናል እንሆ :-

ኢትየኪክ :- ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በስምምነት መለያየቶን ተስሟቷል ? መረጃውን ምን ያህል እውነት እንደሆነ ከእርሶ ለማጣራት ፈልጌ ነበር ?

አሰልጣኝ ፍሰሀ :- እኔም እንደናንተ ነው በማህበራዊ ሚዴያ መሰናበቴን የሰማሁት።

ኢትየኪክ :- ከክለቡ ጋር ያሎት እውነታ ምንድነው ?

አሰልጣኝ ፍሰሀ :- በመጀመሪያ ደረጃ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ በ30 ተሰጠኝ ። የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የሚለው ቲሙን በአስቸኳይ ወደ ውጤት አብቃው የሚል ነበረ። ከዛ በኃላ በስስተኛው ቀን ደግሞ ክለቡ ሊያናግረኝ ስለሚፈልግ ከባህርደር እንደመለስ ተጠየኩኝና ደብዳቤ ሰጡኝ። እና ደብዳው የማስጠንቀቂያ እንጂ ሌላ አልነበረም። እኔም ሶሻል ሜዲያ ላይ ነው ያየሁት። ከማንም ጋር እስከ አሁን አልተገናኘሁም። እኔም ኩላሊቴን አሞኝ ወደ ቢሮሞ አልሄድኩም ። የገባሁትም ከባህርዳር ትላንታ ወደማታ ላይ ነው። ማታ ደግሞ አሞኝም ነበር ። አሁን ደግሞ ልክ እንዳንቺ ነው የሰማሁት ።

አሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን

ኢትየኪክ :- ስለዚህ የተባለው መረጃ ትክክል አይደለም ወይስ መረጃው ትክክል ነው ይላሉ ?

አሰልጣኝ ፍሰሀ :- እኔ ምንም የማወቅ ነገር የለም ። በስምምነት ለሚለው ቃል። ማታ ነው ከባህርዳር የመጣሁት ከማንሞ ጋር እስካሁን አልተገናኘሁም።

ኢትየኪክ :- ግን አሁን ባለው ሁኔታ የመመለሶት ነገር ያበቃ ይመስላል :በቃጣይ ያሰቡት ነገር ካለ ? ቀጣይ ማረፊያ ክለበ?

አሰልጣኝ ፍሰሀ :- ከዚህ በኃላ የመመለሱ ነገር አይኖርም። በቀጣይ ደግሞ የአሰልጣኝ ህይወት እንደነበረው ይቀጥላል …(ፈገግታ) የተለያዩ ክለቦች የጠየቁኝ አሉ። በቤትኪንግ ፕሪምየር እንዲሁም በከፍተኛ ሊግ አሉ የጠየቁኝ። በቀጣይ አመት ደግሞ እንመለሳለን ….

ኢትየኪክ :- በሚሰጧቸው አስተያየቶች የሱፐር ስፖርት ተመልካች ተወዳጅ ነበሩ :ይሄ ሊቋረጥ ነው ማለት ነው?

አሰልጣኝ ፍሰሀ :- በፈገግታ አዎ። የዲ.ኤስ ቲቪ ህይወት ነበርኩ። ምን ያደርጋል። “አትሩጥ አንጋጠህ” ይላሉ እናቶች ሲተርቱ …. የኢትዮጵያ እግርኳስም በቃ እንደዛ ነው ። በቅርቡ ሱፐር ስፖርት ጠርተውኛል እኖራለሁ። ግን ከዛ ውጭ በዚህ አመት በቤትኪንግ የለሁም።

ኢትየኪክ :- አመሰግናለሁ ምላሾን ስለሰጡኝ

አሰልጣኝ ፍሰሀ :- እኔም ስለጥያቄዎችሽ አመሠግናለሁ።