ዜናዎች

-አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ የዋሊያዎቹ ይፋዊ አሰልጣኝ ሆነው ዛሬ ስምምነት ፈፅመዋል!

“በ15 ቀን ውስጥ ተአምር መስራት አልችልም”

                                        – አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ

👇
አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ የዋሊያዎቹ ይፋዊ አሰልጣኝ ሆነው ዛሬ ስምምነት ፈፅመዋል። አሰልጣኙ በአንድ ዓመት ውል 250ሺህ፡የወር፡ደሞዝ የመድንን ክለብም ሳይለቁ ደርቦ የሚሰሩ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ የሚያደርጋቸውን ሁለት የሜዳው ጨዋታዎችን ሞሮኮ ላይ ያከናውናል።
የመጀመርያው ጨዋታ ከሴራሊዮን ኅዳር 5 ፣ ሁለተኛው ጨዋታ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ኅዳር 11 የሚደረግ ሲሆን ሁለቱም ጨዋታዎች በሞሮኮ አል ጀዲዳ ከተማ የሚገኘው ኤል አብዲ ስታዲየም የሚደረጉ ይሆናል. ብሄራዊ ቡድኑን በኢንተርናሽናል ውድድር ተፎካካሪ ማድረግ የሚጠብቅባቸው አሰልጣኝ ገብረመድህን ዛሬ ምሽት ለቀጣይ ጨዋታ የተመረጡ ተጨዋቾች ይፋ የሚያደርጉ ሲሆን እሁድ ልምምዳቸውን ይጀምራሉ።
በረፋዱ የስምምነት ሂደት ላይ እንደተገለጸው ብሔራዊ ቡድኑ አንድ የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።
በአንፃሩ አሰልጣኙ በዛሬው ስምምነት ይህን ብለዋል ” የማያሳፍር ውጤት በሁለት ጨዋታ እንዳይመዘገብ እጥራለሁ” ካሉ በኃላም ሊያግዙኝ፡የሚችሉትን ረዳቶችን እመርጣለሁ ” ብለዋል