ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” አሰልጣኜ ቀይሮ ሲያስገባኝም ጎል ታገባለህ ነው ያለኝ፣ እሱ በሰጠኝ ማበረታታት ነው ጎል ያስቆጠርኩት” ዱሬሳ ሹቤሳ

የሰበታ ከተማው ዱሬሳ ሹቤሳ ተቀይሮ ገብቶ ሰባታን ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ አድርጓል። ተጨዋቹ ከዛሬው ከጨዋታ በኃላ ከሱፐር ጋር ቆይታ አድርጓል።
ተቀይረህ ስትገባ ምን እያሰብክ ነበረ?
“ቡድናችን ካለበት ውጥረት አንፃር ጥሩ ዞን ላይ አልነበርንም። ይሄን የመሠለ ቡድን ደግሞ እዚህ ደረጃ ላይ መሆን ስለሚያስቆጭ ከዛ አንፃር ስነበር በቁጭት ነበር የገባሁት። የተሻለ ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ነበር የገባሁት እግዚአብሔርም ረድቶኛል”
ስለ ጎላ መቆጠር
” ኳሳን መጀመሪያ ማማዱ ጨርሶ ነው የሰጠኝ ። ከእኔ ጋር የሚጫወቱ ጓደኞቼ ልምድ ያላቸው ናቸው ፣ በሳልም ናቸው። የቡድናችን አጨዋወት ለእኔ የሚመቸኝ ነው። አሰልጣኛችን ያለበት ስራ በጣም ጎበዝ አሰልጣኝ ነው እናንተም እንደምታውቁት አሉ ከሚባሉ አሰልጣኞች አንዱ ነው። ከእሱ አንፃር ያለንበት ቦታ አይገባንም ነበር። የእሱ ነገር ይህን እንዳረግ ገፋፍቶኛል ለዛም ነው ደስታ አገላለጽም እሱ ጋር የሄድኩት”
ተቀይሮ ሲገባ አሰልጣኙ የነገረው ?
” አሰልጣኜ ቀይር ሲያስገባኝም የተከላካይ ክፍሉን እያገዝክ ጎል ታገባለህ ነው ያለኝ። እሱ በሰጠኝ ማበረታታት ነው ጎል ያስቆጠርኩት”