አትሌቲክስ ዜናዎች

አረንጓዴው ጎርፍ በአክራ ሰማይ ስር ተከታለው በመግባት አሸንፈዋል !

👇
 
በጋና አክራ የ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድንቅ ብቃታቸውን አሳይተዋል
በ5000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ተከታለው ገብተዋል
🥇መዲና ኢሳ 🇪🇹
🥈ብርቱካን ሞላ🇪🇹
🥉መልክናት ውዱ 🇪🇹
በወንዶች የ3000 ሜትር መሰናክል ፍፃሜ ለሃገራችን የወርቅ ሜዳልያ በአትሌት ሳሙኤል ፍሬው ተገኝቷል
🥇ሳሙኤል ፍሬው 8:24.30 ወርቅ
4ኛ አብርሃም ስሜ 8:27.30
5ኛ ሚልኬሳ ፍቃዱ 8:27.55