አፍሪካ ዜናዎች

#አልቢትር ባምላክ ተሰማ የአውሮፓን የፍፃሜ ጨዋታ እንዲመራ ተጋብዟል!

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ ሰኔ 4 ቀን የግብፁ ክለብ አል አህሊ እና የሞሮኮው ክለብ ዊዳድ አትሌቲክስ ጋር የሚያደርጉትን የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ እንዲዳኝ መመረጡ ይታወሳል።
በአፍሪካ ዋንጫ ወሳኝ ጨዋታዎችን እና ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በብቃት በመወጣት የሚታወቀው ኢትዮጵያዊው ባምላክ ተሰማ ከአፍሪካ የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ የመልስ ጨዋታ በኃላ ወደ አውሮፓ ተጉዞ በአምሰርዳምር ከተማ ከ26 – 29 July ለ18ኛ ጊዜ የሚካሄደውን በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን የባሕል እና የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የመዝጊያ የፍፃሜ ጨዋታውን እንዲመራ በክብር እንግድነት መጋበዙን የስፖርት ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
የኢትዮ ኪክ (ሊንኮቻችን)
#አዲሱ የቲክቶክ ገፃችን
#በኢንስታግራም ገጻችንን :-
🔛ድረ ገጻችንን :-