ዜናዎች

“አላዋቂ የሆኑ ለኢትዮዽያ ቡና አንደም ሳንቲም የማይጥሉ መሀይም የሆኑ የፌስቡክ አርበኞች ቦርዱ ነው እንዲህ ያደረገው ይላሉ” መቶአለቃ ፈቃደ ማሞ

የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር እና የኢትዮጵያ ቡና የቦርድ ሊቀመንበር መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ትላንት ረፋድ የብስራት-ስፖርት እንግዳ ቆይታ አድርገው ነበር፡፡መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በቆይታቸው በርካታ ሊጉን የተመለከቱ አስተዳደራዊ ጥያቄዎች እና የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ጥያቄዎች ከብስራት ኤፍ ኤም ስፖርት መንሱር አብዱልቃኒ ጥያቄ ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።
ከቆይታቸው መኸል የክለባቸው እና የአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን ጉዳይ በተመለከተ ከተነሱት ጥያቄዎች እንሆ ……
መንሱር :▪ ” የግል ስራ አሎት ፣ክለብ ይመራሉ እንዲሁም የሀገሪቷን የሊግ ካምፓኒ ቦርድ ይሰበሰባሉ እና…ስራዎት ብዙ ነው። ባለብዙ ደጋፊ ክለብ ብዙ ጥያቄ አለበት ወቀሳም ፣ …. እንደው መቶ አለቃ ቆዳዎት ወፍራም ነው እላለሁ በዚህ ይስማማሉ? “
🔛መቶ አለቃ :-▪” በስፖርት ውስጥ ከ40 ዓመት በላይ ቆይቻለሁ። ኳሱ ላይ 100% የሆነ በሁለቱም አቅጣጫ ብትሸነፍም ብታሸንፍም 100% የሆነ ድጋፍ አታገኝም። ስለዚህ ይህንን ተለማምደን ቆዳዬም ወፍራም ሆኗል። አሁን ግን ወደ መጨረሻው ዕድሜም ላይ ስላለሁ መቀነስ ያለብኝ ይመስለኛል እሱን በቅርብ ጊዜ የሚሆኑት ይሆናሉ። ይሄን እያሰብኩ ነው።
መንሱር:▪ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለመለወጥ ትልቅ ትግል አድረገው አሁን ሊጉ በቴሌቪዥን መብት እስከመሸጥ አድርሰዋል። በዚህ ሊመሰገኑ ይገባል… በርግጥ ይሄ ቅርብ ጊዜ ቢሆንም በኢትዮጵያ ቡና ውስጥ በየጊዜው ጥያቄዎች ይነሳሉ ፣ ቀደም ባሉት ጊዜያት ለኢትዮጵያ ቡና ውጤት አለመስመር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አወዳዳሪ አካላትን ተጠያቂ ያደርጉ ነበር አሁን ደግሞ እርሶ በሚያስተዳድሩት የሊግ ካምፓኒም ኢትዮጵያ ቡና በሚፈለገው መልኩ በተወዳዳሪነት አይገኝም ምክንያቱ ምንድነው ?”
🔛መቶ አለቃ :- ምክንያቱ በጣም ቀላል እና ውስብስብ ያልሆነ ነው። ካለፉት ዓመታት እንነሳ ሁላችንንም የምንስማማበት ያለፉት ዓመታት የእግር ኳስ ውድድሮች ብዙ ጥቁር ነጥቦችን የተሰጡት እና የብዙ ክለቦች ድካምና ልፋት ባዶ የሆነበት፣ ጥቂት ክለቦች ደግሞ በነበራቸው በፌዴሬሽኑ እና በዳኞች ላይ በነበራቸው ተፅዕኖ ምክንያት ውጤታማ ናቸው ተብሎ አልፈናል።
አሁን ሊጉ ከመጣ ወዲህ በተቻለ መጠን የሊጉ ውድድር ለህዝብ ክፍት ነው። ክለቦች ውጤትም የሚያገኙት በልፋት ነው። አልፎ አልፎ የሚታዪ የዳኝነት ችግሮችን ሊጉ እየቀጣ ለማስተካከል እየተሞከረ ነው።
ስለዚህ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቡና ምን ሆኖ ነው ውጤት ያለገኘው ፣ለምንድነው ወገብ ላይ የተገኘው
ለሚለው ትንሽ ወደ ኃላ ሄጄ የተጨዋቾች እና የአሰልጣኞች አደረጃጀቱን ባነሳ ጥሩ ነው። በቅድሚያ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኞች የውጭ አሰልጣኞች እነ ፖፓዲች፣ አንድ ዊሽኪ እንደውም ዊሽኪ እኛ ጋር ከተፈራረመ በኃላ ደቡብ አፍሪካ ለሚገኘው አንድ ቡድን ጠፍቶ ሄዶ ከተፈራረመ በኃላ ተከታትለን ፊፋ ላይ ከሰን አስቀጥተን እኛም የቅጣቱን ገንዘብ አስመልሰናል። ከሱ በኋላ እንደገና ፖፓድችን አመጣን ነገር ግን በሁለተኛው አመጣጡ ላይ ከልብ በሽታ ጋር ችግር ስለነበረበት ለቆ ሄደ ።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለን የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ከትንሽ ልጅ አንስቶ እስከ ትልቅ ወደ ጨዋታችን እንመለስ ። የቡና ጨዋታ የሚባሉት እነ ሱዪም አባተ Introduced ያደረጉት ቡና በአጭር ቅብብል የእግር ኳስ አጨዋወት የሚታወቅ ስለሆነ ወደ እዛው እንመለስ ተባለ።
እንደሚታወቀው በዓለም ላይ ሁለት የአጨዋወት ሂደቶች ነው ያሉት ። አንደኛው Direct Football ሲሆን ሌላኛው Possession Football. ነው ።
እናም ቡና የሚታወቀው በ Possession Football
ነው ። ውጤትም ቢጠፋ ዛሬ ብና ጥሩ ተጫውቷል የሚባለው ያችን የPossession Football ሲጫወት ነወሰ እሱን መልሱል የደጋፊዎች ጥያቄ ነበር ። ከዚህ አንፃር እሱን ማን ይመልሰዋል ሲባል ። በዚሁ በእኛ ቤት ያደገው እና በዚህም ጨዋታ ጥሩ ሲጫወት የነበረው ካሳዬ ይምጣል የሚል የደጋፊዎች ብዙ ጥያቄ ነበር። በጣም ብዙ ጥያቄ
ይህንን ከመወሰናችን በፊት ቦርድ ውስጥ አንድ የቴክኒክ ኮሚቴ አቋቋምን ። የቴክኒክ ኮሚቴ አባላቱ ከውጭም ከቦርድም የተወጣጡ ሆነው ፣ ከቦርዱ አቶ ምኒልክ ከውጭ አቶ አልመዲን ፣ ጌታቸው ቡቡ፣
እና አቶ ዘላለም እነኚ የቦርድ ቴክኒካል ኮሚቴ አባላት ሆነው ተመረጡ።
እነዚህ ጥቂት ስራዎች ከሰሩ በኃላ አቶ ካሳዬ አራጌ ይቀጠሩ የሚል Recommendation ለቦርዱ ይሰጣሉ።
ከዛም ለአቶ ካሳዬ ቅርብ የሆነ ቢሮ መጥቶ እንነጋገራለን። ካሳዬ 1994/95 አሰልጣኝ በነበረ
ሰዓት የታዩ ድክመቶችን ምን እንደነበሩ ነገርኳቸው ። ከዛም ይሄ ቀላል ነው አሉ። ያነሳሁት ነጥብ
1ኛ የPhysical fitness ነበር፣ 2ኛ አቶ ካሳዬ ሲመጣ የምንፈልገው እኛ ወጣት ተጨዋቾች እንዲመለምልልን እና ክለቡ ክለቡ ከከፍተኛ ወጪ የሚድንበትን መንገድ እንዲፈልጉልን ፣ 3ኛ በአሰለጣጠን qualification ምን ደረጃ ላይ ናቸው የሚለውን ተወያየን። ከዛ ደረጃውን በተመለከተ በአሜሪካን አገር ከስፔን የመጡ አሰልጣኞች አሰልጥነዋቸል ከዚህ ውጭ ሌላ ነገር ምንም የላቸውም ሲሉን ግድ የለም እኛ እሳቸው እዚህ ከመጡ አውሮፓም አገር ቢሆን ተላልከን እናሰለጥናል በሚል አቶ ካሳዬ መጡ፣ ተፈራረምን። ከእሳቸው ጋር ለረጅም ጊዜ ይተዋወቁ የነበሩት ከእኛም ጋር የቴክኒካል ኮሚቴ አባል የነበሩትን ሰውዬ በምክትል አሰልጣኝነት እንዲቀጠሩ አድርገው ተጨዋቾች ተመለመሉ።
ምን ያህል አወጣን ነው የመጀመሪያው በየዓመቱ ከምናቅደው በጀት ላይ ትንሽ ገንዘቦች 2 ሚሊዮን፣ 3 ሚሊዮን ይተርፉናል። እነዚህ ገንዘቦች ደግሞ ለምናቀምጠው ለሜዳ ወስደናል። እነዚህን ሜዳዎች ደግሞ በአንድ ጊዜ አይደለም የምንሰራው። በተለያየ ጊዜ ዛሬ ሜዳውን ነገ መቀመጫውን እያን ያቀድነው ለዛ የሚሆን ገንዘብ ነበረ።
የሆነው ምንድነው እንደመጡ 14 ተጨዋቾች እንዲለቁ ነው የተደረገው። የእነዚህ ኮንትራት ያላቸውን ተጨዋቾች ስታባርር ካሳ መክፈል አለብህ ። የመጀመሪያ 3.2 ሚሊዮን ብር ካሳ ከፍለን ተጨዋቾች አስወጣን። በነሱ ምትክ ደግሞ 13 የሚጠጉ ተጨዋቾች በ1.9 ሚሊዮን ብር አስፈረምን።
እነዚህ ሲቀጠሩ 100% አሰልጣኙ የሚፈልጋቸው ፣ የእኛ ጣልቃ ገብነት የነበረው አንድ ተጨዋች አንቀበልም ብለናል ስሙን መጥራት አስፈላጊ አይመስለኝም። ያ ተጨዋች ግን ከቡና ስፖርት ክለብ
በዲሲፕሊን ምክንያት ስንለያይ ከከፈልነው 800ሺህ ብር 600ሺህ ተመላሽ አድርግልን ብለነው አልተሳካም።
መንሱር :▪ ካሳዬ ሲመጣ ኤሊት ተጨዋቾችን ሳይሆን ወጣት ተጨዋቾችን አጎልብቶ ክለቡ ገቢ እንዲያገኝ የሚል ነው ። በዚህ በኩል የካሳዬ በአቡበከር ላይ የነበረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው
መቶአለቃ:▪አቡበከር already የነበረ እንጂ እሱ ያመጣው አይደለም።
መንሱር :▪ መመልመሉን አይደለም እያልኩ ያለሁት ማጎልበቱ ነው ….. 29 ጎሎቹ ተመስጋኝ አሰልጣኙ ነው ። ይሄን ተጨዋች ዋጋውን ከፍ በማድረጉ በኩል የተጫወተው ሚና አሁን አስወጣኝ ያሉትን ወጪ ከዛ በላይ መልሷል ። ይህንስ እንዴት ይመልሱታ?
መቶአለቃ:▪አይ ምንም እኮ ስህተት የለውም። አቡበከርን ለዚህ ማብቃቱን አልተቃወምኩም። የአቡበከር ሽያጭ ገና Materializedአላደረገም።
መንሱር :▪ የአሰልጣኙ ፎርሙላ እናንተን በአንድ በኩል ገንዘብ አስወጣ እና ግን ደግሞ ያንን የሚያካክስ ገቢ አስገኝቷል ማለት ይቻላል?
መቶአለቃ:▪ በአንድ ተጨዋች Yes. በአብዛኛው ተጨዋች No ነው መልሴ ። እርግጥ ለመጀመር ተጨዋቾች ከውጭ ያስፈልገው እንደነበር እኔ አምናለሁ። አላዋቂ የሆኑ ለክለቡ አንደም ሳንቲም የማይጥሉ መሀይም የሆኑ የፌስቡክ አርበኞች ቦርዱ ነው እንዲ ያደረገው ይላሉ። ቦርዱ ካሳዬ አምጧል። አንዱ በቀደም በፌስቡክ “ቦርዱ በቀበረው ጉድጓድ እራሱ ይገባበታል” አለን። እስከዚህ ድረስ የወረደ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች አሉ።
እኛ የምንለው ቦርዱ ለካሳዬ ያለውን አሟጦ አንጠባጥቦ ነው የሰጠውነው ። አሁን ችግሩ ምንድነው ኳሱ ሲሸነፍ አጥፊው ቦርዱ ነው። ሲያሸንፍ ሙገሳው ለካሳዬ ነው። እኔ ለማሳጠር እዚህ ላይ ደጋፊ ነን ብለው የሚከራከሩ ሰዎች ያለበትን ድክመት በሀቅ ቢነግሩት ይጠቅመዋል እንጂ ቦርድን በመሣደብ በማንቋሸሽ አንድ እርምጃ ማራመድ አይችሉም።
መንሱር :▪ ለአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ የሚፈልጋቸውን ተጨዋቾች ይምጣልኝ ማለት ተገቢ ይመስለኛል ፣ ይህን የምለው በዓለም አቀፍ አሰራር ቦርዱ አመነበትም አላመነበትም ማድረግ አለበት። ከዚህ አንፃር ካሳዬ የሚፈልጋቸውን ተጨዋቾች አሟልተናል ብላችሁ ታምናላችሁ?
መቶአለቃ:▪ አዎ አሟልተናል።
መንሱር :▪ እኔ ቅድም ያነሱት ተጨዋች ለምሳሌ ?
መቶአለቃ:▪ እሱ እዳ ያለበት ተጨዋች ነው
መንሱር :▪ይቅርታ መቶ አለቃ ይሄ የተከፈለ ገንዘብ ነው። ለፊርማ ለተጨዋቾቹ የተከፈለ ገንዘቡን
በዲሲፕሊን ጥሰት የተከፈለ ገንዘብን መልስ ማለትስ ይሄ አግባብ መርህ ነው?
መቶአለቃ:▪ I think so
መንሱር :▪ ውላችሁ ላይ አለ?
መቶአለቃ:▪ ተጨዋቹ ውል ላይማ ይኖራል። አጠቃላይ ውሉ ደሞዝ የሚከፈልህ አጠቃላይ ለሰራህበት ነው። ከዛ ውጭ በጨበጣ የሚሰጥ ነገር ሌሎች ክለቦች ውስጥ ይኖር ይሆናል ቡና ውስጥ የለም።
መንሱር :▪ስለ ምክትል አሰልጣኝ ዘላለም አላግባብ ከኃላፊነቱ እንደተነሳ ነው የሚናገረው በArt tv ላይም ክለቡ ስሜን እያጠፋ ነው እያለም ነው። የኔ ጥያቄ መቶ አለቃ ረጅም ጊዜ ስፖርት ውስጥ ቆይተዋል እና ዋና አሰልጣኝ ምክትሌ ይሁን ብሎ ሲመርጥ ቦርዱ ለምን ዘላለም እንዲቀጥል ያላደረገው፣ ወይስ የማናውቀው ሌላ ነጥብ አለ?
መቶአለቃ:▪እኛ አንዳንድ ከደጋፊዎች በኃላ አሳይሃለሁ እንዲሁም ከተጨዋቾች በመጡ ጥቆማዎች አሳይሃለሁ……..
መቶአለቃ ከመንሱር ጋር ለአንድ ሰዓት ተኩል ያደረጉት ቆይታ ትሰሙት ዘንድ እንሆ
👇