ዜናዎች

– ናትናኤል ከዓፄዎቹ ጋር የውል ስምምነቱን ለሶስት አመት አራዝሟል !

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተጠናክሮ ለመቅረብ የነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ እና አዲስ ተጫዋቾችን በማስፈርም ላይ ይገኛል። 2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ባለቤት የሆነውና በካፍ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የሚሳተፈው ፋሲል ከነማ  የናትናኤል ገብረጊዮርጊስ የውል ስምምነት ለሶስት አመት አራዝመዋል።

 በ2013  በዓፄዎቹ  በርካታ ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ ለቡድኑ ወሳኝ ነጥቦችን ያበረከተው ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ በፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ መቆየቱን አረጋግጧል።

እንደሚታወሰው ዓፄዎቹ  ሰሞኑን በአዲስ መልክ አብዱል ከሪም ፣ ኦኪኪ አፎላቢ እና አስቻለው ታመነን በማስፈረም እንዲሁም  የዳንኤል ዘመዴ ፣ ኪሩቤል ሀይሉ፣ ሚካኤል ሳማኪ እና ከድር ኩሊባሊን ውል ማራዘማቸው አይዘነጋም ።