አፍሪካ ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚያካትተው  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና  የአሜሪካ ጉዞ  !

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው ሐምሌ ወር  ወደ አሜሪካ ተጉዞ ሐምሌ 26 ከጉያና ብሔራዊ ቡድን እና ሀምሌ 29 ከአትላንታ ዮናይትድ ክለብ ጋር  የሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ የፌዴሬሽኑ ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን  እና የወዳጅነት ጨዋታውን ያዘጋጀው  በፊፋ እውቅና ያለው   የጨዋታ አገናኝ ሲጂኤ ኒውማን በመወከል  አቶ ዳዊት አርጋው  ሰፋ ያለ መግለጫን በጋራ  ሰጥተዋል

                                  አቶ ባህሩ ጥላሁን

በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በኩል አቶ ባህሩ ጥላሁን እንደገለፁት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን   ሲጄኤ ኒው ማን ከተሰኘ  በፊፋ እውቅና ያለው   የጨዋታ አገናኝ ነዋሪነቱን  በሀገረ አሜሪካ ካደረገው ካምፓኒ ባለቤት ጋር ውይይቶች ማድረግ ከጀመረ አንድ ዓመት ማስቆጠሩን በመጥቀስ መግለጫውን ጀምረው  በመቀጠልም  ነሐሴ ወር አካባቢ ከአቶ ዳዊት ጋር  ከተገናኙ በኋላ  ሲጄኤ ኒው ማን ከተሰኘው ተቋም ጋር በጋራ በመሆን ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ተጉዞ ጨዋታዎችን እንዲያደርግ  እና የብሔራዊ ቡድኑ ወጪዎች እና በሚያገኘው ጥቅም ዙርያ ለረጅም ወራቶች መወያየታቸውን ተናግረዋል።

አቶ ባህሩ  ብሔራዊ ቡድኑ አሁን ከተገለፀው ብሔራዊ ብድን  በፊት ከሌሎች ብሔራዊ  ቡድኖች ጋር   አማራጮች ለማየት መሞከሩን ጠቅሰው በመጨረሻም ከብዙ ድርድሮች በኃላ አሁን ይፋ ባደረጉት መልኩ እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል።

የፌዴሬሽኑ ፀሀፊ ወደ አሜሪካ የሚጓዘው ቡድን ተጨዋቾች አሰልጣኞች እና  አመራሮችን  ቁጥራቸውም  ከ32 እንደማይበልጥ ጠቅሰው የቡድኑ የትራንስፖርት  እና በቆይታ የሚኖረው ሙሉ  ወጪዎች በሲጂኤ ኒው ማን እንደሚሸፈን ገልፀዋል።

በመቀጠል የወዳጅነት ጨዋታ አዘጋጅ   ሲጂኤ ኒው ማን በመወከል  አቶ ዳዊት አርጋው  እንደተናገሩት  የዚህ ዓይነቱ የወዳጅነት ጉዞ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ መሆን ጠቅሰው  ይህ ጉዞ  እንዲሳካ ከካምፓኒው ጋር በመስማማት ሂደቱን ለማሳካት አንድ ዓመት መፍጀቱን አስታውዋል።

                                       አቶ ዳዊት አርጋው

አቶ ዳዊት በመግለጫው እንደተናገሩት ይህ  ጅምር  ብሔራዊ ቡድኑ የወዳጅነት ጨዋታ ከማድረጉ ጎን ለጎን  በአሜሪካ የሚገኙ እና ለኢትዮጵያ እግርኳስ በስፖንሰርሺፕ ፣ ልማት ግንባታ  መሠል በሆኑ ስራዎች ለመሳተፍ ለሚፈልጉ እንዲሁም በልምድ ልውውጥ እና ተጨዋቾችን ለሙከራ ለሚፈልጉ ካምፓኒዎች ፈር ቀዳጅ  ነው ብለዋል።

በውጪ በኩል አቶ ዳዊት እንዳስታወቁት የጉዞ ሙሉ ወጪ በካምፓኒው እንደሚሸፈን ገልፀው በዚሁ አጋጣሚ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አብሯቸው ሊሰራ ፍቃደኛ መሆኑን  አመስግነዋል።

በመጨረሻም በመግለጫው ለተነሱት ጥያቄዎች  የፌዴሬሽኑ ፀሐፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን  እና የወዳጅነት ጨዋታውን ያዘጋጀው  ሲጂኤ ኒውማን በመወከል  አቶ ዳዊት አርጋው  ምላሽ ሰጥተዋል