ትውልደ ኢትዮጵያውያን

ትውልደ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ- በሊቨርፑል ስኬታማ ጊዜን እያሰለፈ ይገኛል !

ከለምለሚቱ የኢትዮጵያ ምድር በከንባታ ጠንባሮ ተወልዶ ከታላቅ ወንድሙ መለሰ ጋር እድገቱን በጀርመን ያደረገው ትውልድ ኢትዮጵያዊ መልካሙ ፍራውንዶርፍ ለሊቨርፑል በፈረንጆቹ 2020ዓ/ም መፈረሙ ይታወሳል።ትውልደ ኢትዮጵያዊ መልካሙ በሳምንቱ መጨረሻ ሊቨርፑል ከኤቨርተን ባደረገው ከ18 ዓመት በታች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ገና ጨዋታው እንደተጀመረ በ1ኛው ደቂቃ ጎል ማስቆጠር ሲችል በጨዋታው ሊቨርፑል 2 ለ 1 አሸንፎ ወጥቷል።ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ መልካሙ ፍራውንዶርፍ በሊቨርፑል በ“AXA” አካዳሚ ሆኖ በአካዳሚው ፈጣንና የተሳካ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል።