ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

-ትውልደ ኢትዮጵያዊው ግብጠባቂ በካናዳ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ ይገኛል

👇
ትውልደ ኢትዮጵያዊው የ16 ዓመቱ ናትናኤል አብርሀም ለካናዳ ከ 17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ሆኖ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ እየተጫወተ ነው። በሰባት አመቱ እግር ኳስ መጫወት የጀመረው ናትናኤል TFC Academy ቶሮንቶ ፉትቦል አካዳሚ ውሰጥ ተካቷል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ናትናኤል ለካናዳ ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰለፈበት የትላንቱ ጨዋታ ቡድኑ በስፔን 2 ለ 0 ተሸንፏል።
ከእግርኳስ በተጨማሪም የቅርጫት ኳስ እና የዋና ስፖርት የሚያዘወትረው ታዳጊው ግብ ጠባቂ ቁመቱ 1.85 cm ሲሆን የሊዮኔል ሜሲ ፣የፔሌ እና የኤሲ ሚላኑ ግብጠባቂ ማይክ ማግናን አድናቂም ነው። በክለብ ደረጃ ባርሴሎና፣ የባየር ሙኒክ እና ማንቸስተር ሲቲ አድናቂም እንደሆነ ተናግሯል ።
ካናዳ በቀጣይ የፊታችን ሰኞ ከኡዝቤክስታን ሐሙስ ደግሞ ከማሊ በምታደርገው የዓለም ዋንጫ ከ17 ዓመት ማጣሪያ ጨዋታ በግብጠባቂነት በካናዳ ቡድኑ ውስጥ ተካቷል።