ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ- በሊቨርፑል የመጀመሪያውን አዲስ  የኮንትራት ስምምነት አኖረ!

ከለምለሚቱ የኢትዮጵያ ምድር በከንባታ ጠንባሮ ተወልዶ ከታላቅ ወንድሙ መለሰ ጋር እድገቱን በጀርመን ያደረገው ትውልድ ኢትዮጵያዊ መልካሙ ፍራውንዶርፍ በፈረንጆቹ 2020 ዓ/ም ከጀርመኑ ከሆፌንሄም የሊቨርፑልን አካዳሚ መቀላቀሉ ይታወሳል።

የ 17 ዓመቱ ወጣት ባለፈው ክረምት ቀዮቹ የተቀላቀለ ሲሆን የውድድር ዘመኑን ከ 18 ዓመት በታች ቡድኑ ጋር አሳልፏል ፡፡ መልካሙ ፍራንዶንዶፍ በሊቨርፑል “AXA” ማሠልጠኛ ማዕከል የ 2020/21 የውድድር ዘመን ለቡድኑ ወሳኝ ተጨዋች በመሆን ታላቅ ሚና ተጫውቷል ፡፡ በዘንድሮ የ2021 የውድድር ዓመት ተስፋ ከተጣለባቸው ሶስት የሊቨርፑል አካዳሚ ተጨዋቾች አንድ የነበረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ- በሊቨርፑል የመጀመሪያውን አዲስ  የኮንትራት ፊርማውን ዛሬ አኑሯል ።

ትውልድ ኢትዮጵያዊው መልካሙ ፍራውንዶርፍ
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ የአጥቂ -አማካይ መልካሙ ፍራውንዶርፍ ከፊርማው በኃላ በኢንስትግራም ገፁ እንደተናገረው ” ይህን የመጀመሪያውን ፕሮፌሽናል የኮንትራት ስምምነት ለማድረግ በመብቃቴ ለእኔም ለቤተሰቦቼም ትልቅ ኩራት ነው”በማለት ደስታውን ገልጿል። በሊቨርፑል በአዲሱ “AXA” ማሠልጠኛ ማዕከል ከተቀላቀለ በኃላ በዘንድሮ የ2021 የውድድር ዓመት ተስፋ ከተጣለባቸው ሶስት የሊቨር አካዳሚ ተጨዋቾች አንድ መሆኑ ከቀናቶች በፊት ተዘግቧል.። ትውልደ ኢትዮጵያዊ መልካሙ ባለፈው አመት በጀርመን ከ16 አመት በታች ብሔራዊ የቡድን የቡድኑ አምበል እንደነበር ይታወሳል።