ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ማረን ሃይለስላሴ ለስዊዘርላንድ ሱፐርሊግ በከፍተኛ ክፍያ ሊፈርም መሆኑ ተሰማ !

በስዊዘርላንድ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ከ18 ዓመት በታች እስከ 20 ዓመት በየዓመቱ መሠለፍ የቻለ እና በስዊዝ ዋናው ሱፕር ሊግ ስኬታማ ዕድገቶች እያሳየ የሚገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ማረን ሃይለስላሴ ከሁለተኛ ዲቪዚዮን ወደ ሱፐር ሊግ ሊዘዋወር መሆኑ መረጃዎች ወጥተዋል ።
ፍጥነቱና የተለየ የኳስ ጥበቡ ያለው ትውልደ ኢትዮጵያው ማረን የፕሮፌሽናል የእግርኳስ ህይወቱን ጅማሮ በሰዊዝ ሊግ እ.ኤ.አ 2009 ኤፍ ሴ ዙሪክ ካደረገ ባኃላ ኤፍ ሴ ዙሪክ በዋናው ሱፐር ሊግ መሠለፍ ሲጀምር እ.ኤ አ 2017 ዋናው ቡድን ኤፍ ሴ ዙሪክ በሱፐር ሊጉ 2 ለ 1 አሸንፎ እንዲወጣ በማሴቻሉ ታዳጊው የበለጠ የብዙዎችን ኩረት ማግኘት ችሏል።
ማረን ኤፍ ሴ ዙሪክ በኃላም እ.ኤ.አ በ2019 ዓ.ም ለግማሽ ዓመት በራፐርስቪል በተውሶ ቡድኑ በአጠቃላይ ካደረጋቸው 36 ጨዋታዎች መካከል በ35 ተሰልፎ በመጫወት 7 ጎሎች አስቆጥሮ 3 ለውጤት የበቁ ጎሎችን አመቻችቶ በማቀበል ስኬታማ ጊዜ ማሳለፉ አይዘነጋም።
ከስድስት ወር በፊት ደግሞ በሁለተኛ ዲቪዚዮን የሚወዳደረው የቀድሞ ክለቡ ኒው ሻቴል ክሳማክስ ተጨዋቹን የግሉ በማደረጉን መዘገቡም ይታወሳል።
ይሁንና በሚወጡ መረጃዎች ትውልደ ኢትዮጵያዊው የ22 ዓመቱ ታዳጊ ማረን ሃይለስላሴ ከሁለተኛ ዲቪዚዮን ወደ ሱፐር ሊግ ሊዘዋወር መሆኑ ታውቋል።
ማረን ለሱፐር ሊግ ተወዳዳሪ ለሆነው ኤፍ ሲ ሉጋኖን ክለብ በከፍተኛ ክፍያ ሊዘዋወር መሆኑ ሲሰማ የሕክምና ምርመራን በቀጣይ ሳምንት በመጨረስ ፊርማውን የሚያኖር ይሆናል።