ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“ተጫዋቾቹ በሜዳ ላይ ማድረግ የሚገባቸውን ስላደረጉ በዚህ አጋጣሚ ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ”አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም

በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በደረጃ ሰንጠረዡ በ12ኛ ላይ የሚገኘው አዲሱ የጅማ አባ ጅፋር አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ከዛሬው የባህርዳር የመጨረሻ ቆይታቸው በኃላ የሚከተለውን ሃሳባቸውን ለሱፐርስፖርት ሰጥተዋል።አሰልጣኙ የዛሬውን ጨዋታውን አጠቃላይ ሁኔታ በመናገር ሃሳባቸውን ይጀምራሉ ” በዛሬው የፋሲል ትልቁ ጠንካራ ጎን የመጀመሪያ 20 ደቂቃዎች ብዙ ጊዜ በተጋጣሚ ላይ ጫና በመፍጠር ነው የሚጫወቱት። ይህንን ደጀየግሞ ለተጫዋቾቹ ነግሬያቸው ነበር። ከ20 ደቂቃ በኋላ ኳሱን እየተቆጣጠርነው በአካሏቸውንም እዮ በአዕምሮሯነውንም ቀይረን ወደ ሪትሙ እንገባለን የሚል ሀሳብ ነበረ። ነገር ግን ካላቸው የተጫዋች ጥራት እና ጎል አዳኝ ሙጁብ ቃሲም አማካይነት ሁለት ጎሎች አስቆጥረውብናል። ባልተጠበቀ ሰዓት ነው ። እነዚህን ደቂቃዎች ብናልፍ ኖሮ የተሻለ እንቅስቃሴ በሜዳ ላይ ማድረግ እንችል ነበር። ዞሮ ዞሮ በእኛ በኩል እንደምታየው ነው።አብዛኞቹ በጉዳት ላይ ነው ያሉት። ውብሸት በጉዳት ነው የገባው፣ አማኑኤል በጉዳት ነው የገባው እነ ብዙአየሁም በጉዳት ውስጥ አሉ ። በእንቅስቃሴም ውስጥ የተጎዱ ተጫዋቾች አሉ። ያለፉት አምስት ጨዋታዎች በተወሰኑ ተጫዋቾች ነው ለመጫወት የሞከርነው ካለን የተጫዋች ስብስብ አንፃር ማለት ነው። እንግዲህ ምንም ማድረግ አይቻልም በቀሪው በእረፍት ሰዓታችን ሰርተን የቸሻለና አዳዲስ ተጫዋቾች ወደሜዳ አስገብተን ወይም አስፈርመን ለቀጣይ ጨዋታዎች እንዘጋጃለን ብዬ አስባለሁ ” ብለዋል። በሁለተኛው አጋማሽ ያሳዮት የተሻለ መነቃቃትና እንቅስቃሴ በመጀመሪያው አጋማሽ አለማሳየታቸው ከምን የመጣ እንደሆነ አሰልጣኙ ሲመልሱ ” አዎ …የመጀመሪያውን 20 ደቂቃ ተጫውተናል ። ግን እነሱ በጎል ነው የቀድሙን። ባልተጠበቀ ሰዓት ስላገቡብን በእኛ ቡድን ላይ የመበታተን ነገር ነበር። ዞሮ ዞሮ በሁለተኛው አጋማሽ ላይ የእነሱን ተቃራኒ አጨዋወት ይዘን ነበር ወደሜዳ የገባነው። በርግጥ እነሱ ፈጣን እና ረጃጅም ኳሶች ስለሚጫወቱ ኳሱን በቅርበት ሳዬሆን አጠገብ ለአጠገብ እንዲቀባበሉ ነበር የነገርኳቸው እና ያንን ሜዳ ላይ አድርገውታል። በዚህ አምስት ጨዋታዎች ላይ ሳይ ግን ተጫዋቾቹ በሜዳ ላይ ማድረግ የሚገባቸውን የተቻላቸውን ነገር አድርገዋል። ዞሮ ዞሮ በስራ እና በማጠናከር ስራ ላይ ከተጠመድን አሁን ያሉን እድሎች ብዙ ክፉ አይደሉም። ሰርተን እንለወጣለን ብዬ አስባለሁ። ተጫዋቾቼ ግን አቅማቸው የፈቀደውን ስላደረጉ በዚህ አጋጣሚ ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ” በማለት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ተናግረዋል።