ቀጥታ አፍሪካ ዜናዎች

# ብሔራዊ ቡድኑ ከነገ በስቲያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከዲ.ሪ. ኮንጎ ጋር ያደርጋል!

 

በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት ሲጀምሩ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ሐሙስ መስከረም 12 ዲ.ሪ. ኮንጎን አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ ታስተናግዳለች።

ብሔራዊ ቡድኑ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ አሸንፎ ወደ ተከታዩ ዙር የማለፍ ዕድሉን ለማስፋት የእግርኳስ ቤተሰቡ ድጋፍ ያስፈልገዋል። በመሆኑም በዕለቱ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በነፃ በመታደም ለብሔራዊ ቡድናችን የሞቀ ድጋፋችሁን እንድትሰጡ የኢት.እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋብዟኋል።