አፍሪካ ዜናዎች

ባፋና ባፋናዎች በዋልያዎቹ ሁለት ድሎች በፊፋ ደረጃ ታላቅ ለውጥ ማግኘታቸው እየተዘገበ ነው!

ኳታር ለሚካሄደው የ2022 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለት ጨዋታዎችን አድርገው በሁለቱም ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን እ.ኤ.አ ከ2015 በኃላ በፊፋ የወርሀዊ የደረጃ ሰንጠረዥ 12 ደረጃዎች በማሻሻል ከስድስት ዓመታት በኃላ ከፍተኛውን የደረጃ መሻሻል ማሳየቱ ተዘግቧል።
የአሰልጣኝ ሁጎ ብሮስ ቡድን ለደረጃ መሻሻሉ በዋነኛነት በዚህ ወር ኢትዮጵያን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በሜዳዋ 3 ለ 1 በመልሱ ጨዋታ ጆሀንስበርግ ላይ ደግሞ 1 ለ 0 በድምሩ ውጤት 4 ለ1 በማሸነፍ እንደሆነ በሰፊው ተዘግቧል። ባፋና ባፋና በትላንቱ የፊፋ የደረጃ ሰንጠረዥ ከ 73 ኛ ወደ 66 ኛ ደረጃ ከፍ ማለታቸው ለአሰልጣኙን ሁጎ ብሮስ አድናቆት ተችሯቸዋል።