ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“ባህርዳር ከተማ በጣም ጥሩ ስብስብ ነው ፤ እንደ ቡድን ብንጫወት ዋንጫውን እናገኝ ነበር፤ ደጋፊው ከዋንጫ በላይ የሚገባውም ነበረ “-ምንይሉ ወንድሙ

ምንይሉ ወንድሙ - ባህርዳር ከተማ
ምንይሉ ወንድሙ – ባህርዳር ከተማ

ምንይሉ ወንድሙ ለባህርዳር ከተማ ወሳኝ ከሚባሉት ተጨዋቾች አንዱ ነው። ባህርዳር ከተማ ትላንት ለሁለተኝነት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 2 አች ሲለያዩ ምንይሉ ጎል አስቆጥሮ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ያስቆጠራቸውን ጎሎች 6 አድርሷል። ኢትዮኪክ ከምንይሉ ወንድሙ ጋር ቆይታ አድርገናል።

ኢትዮ ኪክ :- የዘንድሮ በሊጉ ያለህ አቋም እንዴት ይገለጻል ?
ምንይሉ :- ዘንድሮ ወደነበርኩበት የበፊት አቋሜ ለመመለስ እየጣርኩ ነው።
ኢትዮ ኪክ :- ያንን እንዳታደርግ እንቅፋቱ ምን ነበር ?
ምንይሉ :- ኮከብ በሚመረጥ ሰአት ጉዳት አጋጥሞኝ ከሜዴ አርቆኝ ነበረ። ነገር ግን አሁን ላይ እግዚአብሔር ይመስገነው ሙሉ ጤነኛ ነኝ።
ኢትዮ ኪክ :- የዘንድሮ የቲማችሁ አቋም በአንተ እይታ እንዴት ነው ?
ምንይሉ :- ባህርዳር ከተማ በጣም ጥሩ ስብስብ ነው። እንደ ቡድን ብንጫወት ዋንጫውን እናገኝ ነበር። አሁን ለሁለተኝነት ለመያዝ ዕድሉ ሙሉ ለሙሉ አልተሟጠጠም ፤ዕድሉ አለን።
ኢትዮ ኪክ :- ለደጋፊዎቻቹ ከእናንተ የሚፈልጉትን አድርገናል ትላለህ ?
ምንይሉ :- ለደጋፊው የሚፈልጉትን አላረግንም። ደጋፊው ከዋንጫ በላይ የሚገባውም ነበረ።
ኢትዮ ኪክ :- በቀሪዎቹ ጨዋታዎች ምን ለማድረግ ታስባላችሁ ?
ምንይሉ :- ምንም እንኳን የሌሎቹ ውጤት ወሳኝ ቢሆንም በእኛ በኩል ቀሪ ጨዋታዎቹን ሁሉንም ለማሸነፍ ነው ወደ ሜዳ የምንገባው። ከፈጣሪ ጋር ።
ኢትዮ ኪክ :- ከዛ አንፃር ፣የቤትኪንግ ውድድር ስንተኛ ሆነን እናጠናቅቃለን ትላለህ?
ምንይሉ :- ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ
ኢትዮ ኪክ :- ብዙ ጊዜ ማዳ ውሰጥ ስፖርታዊ ጨዋነት የተላበሱ ነገሮች ስታደርግ ትስተዋላለህ ባህሪህ ነው ?
ምንይሉ :- እኔ በጣም ስሜታዊ ነኝ ሜዳ ውስጥ ስገባ ፤ ግን ብናደድም በሜዳ ውስጥ ለተቃራኒ ቡድን ተጨዋች የሆነ መልካም ነገር ደግነትም እንዲሁ አደርጋለሁ። ሁላችንም የሰው ልጆች እንሳሳታለንና መልካም የሚባል ማንነት አለኝ ብዬ አስባለሁ።
ኢትዮ ኪክ :- ከክለብህ ጋር ኮንትራት መቼ ያልቃል ?
ምንይሉ :- በዚህ ዓመት ሰኔ 30
ኢትዮ ኪክ :- ምን ታስባለህ ?
ምንይሉ :- እስካሁንም የተለየ ሃሳብ የለኝም።
ኢትዮ ኪክ :- በዚህ አጋጣሚ ለደጋፊዎቻቹ የምትላቸው ?
ምንይሉ:- ደጋፊዎቻቸውን እንደተለመደው ትዕግስተኛ እንዲሆኑ እና የተሻለ ጊዜ እንደሚመጣ ።