ዜናዎች

“በግብፅ ሁለት ክለቦች   ከሀገር ወጥቶ ለመጫወት ዕድል አግኝቼ ነበር ….ይሳካል ብዬ  ተስፋ አደርጋለሁ ”  – ስንታየሁ መንግስቱ (ወላይታ ድቻ )

 

 

 

የ2014 የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተጠናቀው የአምስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ ይቀጥላል።

በአራተኛው ሳምንት  ከተደረጉት ስምንት ጨዋታዎች ሶስቱ  በአቻ ውጤት  አምስቱ ደግሞ በመሸናነፍ የተጠናቀቁ ሲሆን ከእነዚህ ጨዋታ ውስጥ የጦና ንቦቹ ኢትዮዽያ ቡናን ያሸነፉበት ጨዋታ አንዱ ነው። በተለይም በወላይታ ድቻ   የአጥቂ ስፍራ ደምቆ ከታዮ  ተጨዋቾች መካከል ስንታየሁ መንግስቱ ዋንኛው ተጠቃሽ ሲሆን  የጦና ንቦቹ  3 ለ 1 ኢትዮዽያ ቡናን  እንዲያሸንፉ  የፊት መስመሩ ላይ ትልቁን ሚና ተጫውቶ ሁለት ጎሎችንም አስቆጥሯል።

እናም ይህ ድንቅ አጥቂ ስንታየሁ መንግሥቱ  በግብፅ ክለቦች  መፈለጉን እና  በወቅታዊ አቋሙ ላይ ኢትዮኪክ  ጋር ቆይታ አድርገናል እንሆ :

ኢትዮ ኪክ:-    የዘንድሮ የ2014 ቤትኪንግ በስንታየሁ እይታ እንዴት እየሄደ ነው ?

ስንታየሁ :-ፈጣሪ ይመስገን  በጥሩ እየሄደ ነው ። እስካሁን አሪፍ ነው ማለት እችላለሁ።

ኢትዮ ኪክ:- እንደጠበከው ነበር  የ2014  ጅማሮው ?

ስንታየሁ :- በርግጥ ለእኔ እነዳሰብኩት  ሙሉ ለሙሉ እየሄደ  አይደለም  ።

ኢትዮ ኪክ:- እንዴት  ነው እንደጠበቀው ያልሄደው?

ስንታየሁ :- ማለቴ  …ትንሽ  ከጤንነቴ ጋር በተያያዘ ጉዳት አጋጥሞኝ ነበር። እናም ከዛ አኳያ ለእኔ   እነዳሰብኩት ባይሆንም ግን ደግሞ እንደ ቡድን  ጥሩ ውጤት እና  አሪፍ ነገር እየሰራን በመሆኑ ይሁን ብያለሁ።

ኢትዮ ኪክ:-ጤንነትህ አሁን ላይ እንዴት ነው  ?

ስንታየሁ : – አሁን ጤንነቴ  ጥሩ ነው።  እግዚሐብሔር ይመስገነው እየተሻለኝ ሄዶ አሁን  በጣም ጥሩ ላይ  ነኝ።

ኢትዮ ኪክ:-  በአራተኛው ሳምንት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር  ያሳየኸውን ድንቅ ብቃት እንዴት ትገልፀዋለህ?

ስንታየሁ : –  ከጨዋታው ብጀምር ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያደረግነው ጨዋታ በጣም  ጥሩ ነበረ።  በተለይ በዘንድሮው የሊጉ የመጀመሪያ ጎሌም ስለነበር ልዪ ስሜት አለው።


ኢትዮ ኪክ:-   በጨዋታው ኢትዮጵያ ቡና  እናሸንፋለን ብለህ ገምተህ ነበር ?

መንግስቱ :-  አዎ ! ኢትዮዽያ ቡናን እናሸንፋለን ብለን ነበር የገባነው።እንደውም በጨዋታው ሐትሪክ ብሰራ ደስ ይለኝ ነበር።

ኢትዮ ኪክ:-   የዘንድሮ ከፍተኛ ጎል አግቢዎች ገና ገፍቶ አልተለየም እንዴት ነው  ስንታየሁ እሆናለሁ ብለህ ታስባለህ ?

መንግስቱ :-  እንደፈጣሪ ፍቃድ አዎ ዘንድሮ ኮከብ ጎል አግቢ እሆናለሁ።

ኢትዮ ኪክ:-   ወደ ግብፅ ክለብ ሄዶ ለመጫወት  ዕድሎች አግኝተህ ነበር ስለሚባለው ንገረኝ ?

መንግስቱ :-   አዎ። የግብፅ ሁለት ክለቦች   ከሀገር ወጥቶ ለመጫወት ዕድል አግኝቼ ነበር ፣ ነገርግን ሁሉ ነገር ጨርቼ እስካሁን ቪዛ ባለማግኘቴ አልተሳካም።  እናም ይሄ ነገር ትንሽ አናዶኛል። ግን ከፈጣሪ ጋር ዘንድሮ ጥሩ ጊዜ አሳልፋለሁ።

ኢትዮ ኪክ:-  የግብፅ ማን የሚባለው ክለብ ?መ

መንግስቱ :-  የቀድሞ የሽመልስ በቀለ  ክለብ ምስር አል መቃስ እና አሁን ሽመልስ የሚጫወትበት አልጎውናን ክለቦች ናቸው።

ኢትዮ ኪክ:-  በቀጣይስ ከክለቦቹ ጋር  የውጭ ዕድሉ ይቀጥላል ?

መንግስቱ :- አዎ! ኤጀንቴ እየሰራበት ነው ።  እንደ እግዚሐብሔር ፍቃድ በቅርብ ጊዜ ይሳካል ብዬ  ተስፋ አደርጋለሁ።

ኢትዮ ኪክ :-  ያሰብከው እንዲሳካ ምኞታችን ነው !