ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“በዚህ ማሊያ ይህን ክብር በማሳካቴ ደስታዬ ወደር የለውም፥ ለስኬቱ ሁላችንም አንድ መሆናችን ነው”-ቢኒያም በላይ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

የቅዱስ ጊዮርጊሱ ድንቅ ተጨዋች ቢኒያም በላይ የዘንድሮው የ2015 የውድድር ዓመቱን በስኬት ካሳለፉ ጥቂት ተጨዋቾች መካከል አንዱ ነው። ቢኒያም ፈረሰኞቹን ከመቀላቀሉ በፊት በታዳጊነት ዕድሜው በአውሮፖ ክለቦች የመጫወት ዕድል አግኝቶ የእግር ኳስ ሕይወትን ተሞክሮ በሚገባ የተጠቀመበት ተጨዋችም ነበር ለማለት ይቻላል።

ቢኒያም በላይ-(ቅዱስ ጊዮርጊስ)

በጀርመን ቡንደስሊጋ 2 ተሳታፊ በነበረው ዳይናሞ ደረስደን ከሙከራ ጊዜ በኃላ በኃላም ቢኒያም በአልባኒያው ስኬንደርቡ እንዲሁም በስዊድንቹ ስሪያንስካ እና ለኡመያ ክለቦች በፕሮፌሽናልት ህይወቱን አሳልፏል።
ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላም ባለፉት ሁለት ዓመታት በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ሲዳማ ቡና እና መከላከያ ከጥቂት ወራቶች ቆይታ በኋላ የ2015 የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን በመቀላቀል በየጨዋታው በመሃል ሜዳዉ እና በመስመር ላይ የተሰጠዉን ድርሻ በብቃት በመወጣት በብዙዎች አድናቆት አትርፏል።

በውድድር ዓመቱ ቢኒያም በሜዳ ዉስጥ እና ከሜዳ ውጭ የእግርኳስ ድሲፕሊን በሚያዘው መልኩ ስነምግባር እና ኳስን አጣምሮ በመያዝ ለብዙ ታዳጊዎች ተምሳሌት ይሆናል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የ2015 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒየንስ መሆኑን ተከትሎ ተጨዋቹ የ2015 ዕጩ ኮከብ ተጨዋች ምርጫ ውስጥ  ከታጩ ተጨዋችም አንዱ ሆኗል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የ2015 ቻምፒየንስ መሆኑን ተከትሎ ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈውን ቢኒያም በላይ  ኢትዮኪከ የተሠማውን ደስታ እንዲያካፍለን ጠይቀነው  ሲመልስ” ቡድንኑን ስቀላቀል ሻምፒዮን የማድረግ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ተጨዋቾች አንዱ ነበርኩ እናም ዓመቱን በሚገባ ተጠቅመን  አሁን ላይ ሻምፒዮና መሆኑን አሳክተናል” ካለ በኃላ ” እውነት ለመናገር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቻምፒየንስ በመሆኑ የተሰማኝን የደስታ ስሜት ለመግለጽ ከባድ ነው ብሏል ፣በፈገግታ የተሞላው ቢኒያም በላይ።

 

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በአጭር ጊዜ ቆይታ  የተሳካ ጉዞ ላይ ደርሰሃል ፣  ከዚሁ ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ምን የተለየ ስሜት አለው ለሚሉት ጥያቄዎች ቢኒያም ሲቀጥል ” እውነት ለመናገር ክለቡን ከተቀላቀልኩበት ቀን ጀምሮ አመራሩ ፣ አሰልጣኞቹ፣ ሙሉ ተጨዋቾቹ ወንድሞቼ ነበሩ ። ከዚሁ ጋር ፍቅር የሆኑት የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎቻችን ለድሉ ተጠቃሽ ናቸው። በዚህ ማሊያ ይኸን ክብር በማሳካቴ ደስታዬ ወደር የለውም። በቆይታ በጣም ደስተኛ ነኝ። ለስኬቱ ሁላችንም አንድ መሆናችን ነው። ። በዚህ አጋጣሚ ሁሉም ለሰጡኝ ፍቅር ፈጣሪ ያክብርልኝ እወዳችኋለሁ” ብሏል

የ2015 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዕጩ የኮከብ ተጨዋች ምርጫ ውስጥ ስለመካተቱ እና ዘንድሮ የኮከብ ተጨዋችን ክብር ታሸንፋለህ ለሚለው ሲመልስ ” እንግዲህ ፈጣሪ ያውቃል፥ ነገር ግን የእኛን ክለብ ደጋፊዎች እንደዚሀም የተለያዩ ክለብ ደጋፊዎች ይህን መልካም ምኞታችሁን ስሳላያች በፈጣሪ ስም እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ ።”  በማለት ምላሽ ሰጥቷል

በቀጣይ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የአፍሪካ ሻምፒዮን ሊግ ማጣሪያ ጨዋታ ይጠብቃቸዋል ይህን ለማሳካት በግልህ ምን ታስባለህ ለሚለው ሲመልሰ” እውነት ነው በቀጣይ ለቻምፒዮስ ሊጉ ጥሩ ዝግጅት የምናደርግበት እና ክለባችን በቻምፒየንስ ሊጉ ላይ ትልቅ ታሪክ የምንሰብርበት ጊዜ ነው ፣ይህን ለማሳካት ጠንክረን እንሰራለን።” በማለት የቅዱስ ጊዮርጊሱ ቢኒያም  በላይ ሰ ተናግሯል