ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

በዕድሳት ላይ የሚገኘው የድሬዳዋ ስታዲየም ዛሬ ምልከታ ተደርጓል!

🕳ከ9ኛው ሳምንት በኃላ የሊጉን ጨዋታን ያስተናግዳል!
👇
የ10ኛውን የአፍሪካ ዋንጫና አገራዊ ያስተናገደው ታሪካዊው የድሬዳዋ ስታዲየም የፊፋን ስታንዳርድ የጠበቀ ኢንተናሽናል ስታደየም ለማድረግ የዕድሳት ስራው በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል።
በተለይም ዘመናዊ በሆነ እና የፊፋ ሁሉንም መሥፈርቶችን ባሟላ ደረጃውን በጠበቀ ሳር የማልበሱ ሂደት እየተጠናቀቀ መሆኑን ባላፈው ዘገባችን ባስነበብናቹ መሠረት አሁን ላይ ሳር የማንጠፉ ስራ ወደ መጠናቀቁ ደርሷል።
በየትኛውም የአየር ሁኔታ ማጫወት በሚችል ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ ( ሀይብሪድ ሣር ) ዘመናዊ መልኩ ሜዳውን የመቀየር ስራው እየተካሄደ ሲሆን የስታዲየሙ ስራዎች ሲጠናቀቁ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ከ9ኛ ሳምንት በኃላ የሚያስተናግድ ይሆናል። በተጨማሪም ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችም የሚያስተናግድ አቅም እንደሚኖረው ታውቋል።
ለአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲሁም ሌሎች ስታዲየሞች ትልቅ ተምሳሌት የሚሆነውን የድሬደዋ ስታዲየም የዕድሳቱ ሚና ስራ እንዲሳካ እያደረጉ ያሉት ከንቲባው ከድር ጁሃር እንዲሁም የወጣቶችና ስፖርት ኮምሽን ኮሚሽነር ፍራኦል ቡልቻ ፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ግንባታውን በመውሰድ እየሰራ የሚገኘው ታን ኢንጂነሪንግ ባለቤት የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ፉአድ ኢብራሂም እንዲሁም የመገናኛ ቡዙኀን ባለሙያዎች በተገኙበት የሜዳውን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ በዛሬው ዕለት ተደርጓል።