አፍሪካ ዜናዎች

#በዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ምክንያት ቤትኪንግ ሊግ ይቋረጣል !

 

 

በኮትዲቯር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ  የማጣሪያ ጨዋታ ዋልያዎቹ ከማላዊ ጋር የሚያደርጉት የጨዋታ እየተቃረበ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ የምድቡ አምስተኛ መርሐ-ግብር ሲሆን፣ ጨዋታው ሰኔ 13 / 2015 (June 20) ይካሄዳል።

አብዛኞቹ የአፍሪካ አገራትም በቀጣይ ከሁለት ሳምንታት በኃላ ለሚያደርጉት ወሳኝ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ዝግጅት የጀመሩም አሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በሦስተኛው እና በአራተኛው የምድቡ ጨዋታ በድምር ውጤት 5 ለ 2 ያሸነፈው የጊኒ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ከግብፅ ጋር ለሚያደርገው የምድቡ ጨዋታ ዛሬ ተጨዋቹ ለዝግጅት ሆቴል ገብተዋል።

ዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ አምስተኛ የምድብ ጨዋታቸውን ሰኔ 13 ለማከናወን አዲስ የተመረጡት አሰልጣኞች በቀጣይ ሳምንታት የተጨዋቾች ምርጫ  ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለዚህ ጨዋታም የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ነገ ተጀምሮ ከሚደረገው የ28ኛው ሳምንት ጨዋታ በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባለበት የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ  ሊጉ የሚቋረጥ ይሆናል።

እንደሚታወሰው ዋልያዎቹ የራሳቸው ሜዳ ባለመኖራቸው የሜዳ ጨዋታቸው በሞዛምቢክ ሜዳ እንደሚካሂዱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀድሞ ለካፍ ማሳወቁ አይዘነጋም።