ዜናዎች

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ለታዳጊ ቡድኑ አባላት የምስጋና ግብዣ አደረጉ !

 የኢትዮጵያ ከ 17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን
 የኢትዮጵያ ከ 17 አመት በታች ብሔራዊ  የእግር ኳስ ቡድን ወደ እስራኤል ተጉዞ የወዳጅነት ጨዋታ ከእስራኤል ከቻቸው ጋር  ባለፈው ሰኔ ወር ማድረጋጭቸው ይታወሳል።
ይህን ታሪካዊ የወዳጅነት ጨዋታ ላደረጉት ታዳጊዎች እና ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባለሥልጣናት የምስጋና የምሳ ግብዣ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ተደርጓል።
በመክፈቻ ንግግራቸው አምባሳደር አድማሱ ለቡድኑ የእንኳን ደስ ያለችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በቅርቡ ያደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ በታሪክ የመጀመሪያው እና በዘርፉ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ቀጣይ ያለው መሆኑን ያጠናከረ ነው ብለዋል ፡፡የወዳጅነት ጨዋታው የበለጠ የማይረሳ ለማድረግ ከኢትዮ-እስራኤል የዲፕሎማሲ ግንኙነት 30 ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ጋር የተዛመደም እንዲሆን መደረጉን አመልክተዋል ፡፡
ይህን ለማስታወስ አምባሳደር አድማሱ በቁጥር 3️0️ የሆነ ማሊያን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አበርክተዋል ፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጂራ በበኩላቸው በኤምባሲው እየተደረገ ያለውን አቀባበል እና ጥረት በማድነቅ ፌዴሬሽኑ በመስኩ ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡ በኢየሩሳሌም የተፈረመውን ስምምነት በማስታወስም ፌዴሬሽኑ ከእስራኤል ከፍተኛ የአቅም ግንባታ ፣ የአሰልጣኞች ትምህርት ፣ ስፖርት እና ሌሎችም ጉዳዮች ፌዴሬሽኑ ልምድ ለመቅሰም ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል