ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ቦታ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ቀጣይ የመድን አሰልጣኝ ?

አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ

 

የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ መሆኑ እየተረጋገጠ ባለበት አሁን ላይ በአሰልጣኝ ገብረመድህን ቦታ መድኖችን ማን ይረከባል የሚለው ሌላው ትኩረትን የሳበ ጉዳይ ሆኗል።

ኢትዮኪክ ባገኘችው የታማኝ ምንጮ መረጃ መሠረት የመድን የክለቡ የበላይ ኃላፊውች በአሰልጣኝ በገብረመድህ ኃይሌ ቦታ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማሪያምን አልያም አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን መፈለጋቸው ቢሰማም በአንፃሩ አሰልጣኝ ፀጋዬ ለረጅም ጊዜያት በክለብ አሰልጣኝነት የራቀ ከመሆኑ አንፃር አሁን ላይ ክለብ የማሰልጠን ፍላጎት እንደሌለው ተሰምቷል። ነገር ግን የአሰልጣኝ ፀጋዬ ፍላጎት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ዋልያዎቹን የሚረከብ ከሆነ አብሮ የዋልያዎቹ ምክትል አሰልጣኝ የመሆን ፍላጎት እንዳለው መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በሌላ በኩል መድኖች ውጤታማ አሰልጣኛቸው ገብረመድህን ኃይሌ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ የሚሄድ ከሆነ በምትኩ ከያዟቸው አሰልጣኞች መካከል ካሣዬ አራጌ ይገኝበታል።

አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ከኢትዮዽያ ቡና ከተለያዩ በኃላ በዕረፍት ላይ ይገኛል። እንደሚታወሰው አሰልጣኝ ካሳዬ የባለፈው የዝውውር ገበያ ላይ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ ተያይዞ የነበረ ቢሆንም ካሳዬ አሁን ላይ ለመድን ከታጩት አሰልጣኞች አንዱ ሆኗል።

እንደተባለው ሆኖ አሰልጣኝ ካሳዬ መድንን ከተረከበ በተጨዋችነት እና በአሰልጣኝነት መድንን ለማሰልጠን ዕድል ያገኛል ማለት ነው. እንደሚታወሰው ካሳዬ በተጨዋችነት ዘመኑ ለኪራይ ቤቶች፣ ለኢትዮጵያ ቡና እና ለመድን ተጫውቷል። ካሳዬ በተጨዋችነት 1987 ዓ.ም ለአንድ ዓመት ለመድን ተጫውቶ ከዛ በኃላ በ 1988 ወደ ኢትዮጵያ ቡና የገባው። ስለዚህ ካሳዬ ኢትዮ- መድንን የሚረከብ ከሆነ በአሰልጣኝነት እና በተጨዋችነት ዘመኑ ኢትዮጵያ ቡናን እንዲሁም መድንን በማሰልጠን ሌላ የራሱን የታሪክ ምዕራፍ ይከፍታል ማለት ነው።