ዜናዎች

– ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የተሳተፈበት ጨዋታ በሜክሲኮ 4 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል !

በቶኪዮ ኦሎምፒክ  ሜክስኮ  ፈረንሳይን 4 ለ 1  ያሽንፈችበት ጨዋታ
በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ኢትዮጵያ  ከምትሳተፍባቸዉ የስፓርታዊ  ውድድሮች  በተጨማሪም  በእግር ኳስ ባለሙያም ተወክላለች። በቶክዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በእግር ኳስ ዳኝነት የወከለው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ዛሬ ረፋዱን የተደረገውን የወንዶች እግር ኳስ የምድብ ” ሀ ” ፈረንሳይ  ክ ሜክስኮ ጨዋታ በ4ኛ ዳኝነት መርቷል።
ጨዋታውን በዋና ዳኝነት አውስትራሊያዊውያኑ ዋና ዳኛ ክሪስ ቤዝ እንዲሁም ፣ አንቶን ሽቼቲኒን ( 1ኛ ረዳት ዳኛ ) ፣ ጆርጅ ላክሪንዲስ (2ኛ ረዳት ዳኛ)  የመሩት ሲሆን ኢትዮጵያዊው ባምላኩ ተሰማ  የጨዋታው4ኛ ዳኛ ሆነው  መርተዋል። በጨዋታው የቫር ዳኝነቱን ሚንግ ፉ ከቻይና እና አብዱልቃድር ቢትገን ከቱርክ ረዳት የቪዲዮ ረዳት ዳኛ በመሆን በጥምረት ዳኝተዋል።  ይህን ጨዋታው ሜክስኮ  ፈረንሳይን 4 ለ 1  አሽንፋለች ።