ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” በትክክል የጀማልን መውጣት አይቼ ነው ጎሉን ያስቆጠርኩት  ” ግርማ ዲሳሳ

የባህርዳር ከተማ የዛሬውን ጨዋታ ሁለት ለባዶ ሲያሸንፍ የፕሪምየር ሊጉን ድንቅ ጎል ያስቆጠረው ግርማ ዲሳሳ ከጨዋታው በኃላ ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ አድርጓል.
ስለ አስቆጠረው ጎል
” በትክክል የጀማልን መውጣት አይቼ ነው ያንን ዐድል ነው የተጠቀምኩት እና ያስቆጠርኩት ።
በጨዋታው ተደጋጋሚ ሙከራ እና የቡድኑ ጥረት
” ከእኛ በፊት ያሉት ቡድኖች ነጥብ ስለጣሉ በዛ ተነሳሽነት ፈጥረን ነው ወደሜዳ የገባነው። በመጀመሪያ ያንን ከጓደኞቼ ጋር ተጋግዘን ውጤት ልንይዝ ችለናል።
ቡድኑ ወደ ሚፈልገው መስመር እየመጡ ስለመሆኑ
” አዎ ። በትክክል ውጤታችን የሚያሳየውም አምስት ጨዋታ ወይም ስድስት ጨዋታ ተከታታይ ነጥብ የያዝንበት በመሆኑ ወደ ምንፈልገው መሥመር መጥተናል ብዬ አስባለሁ።
ስለዛሬ ጨዋታው እና ተጋጣያቸው ወልቂጤ
“አሰልጣኛችን ከጨዋታው በፊት ትልቅ ነገር ነግሮን ነበረ። ከዛ በመነሳት ነው እኛም የተጫወትነው።