የ2013 ዓ.ም የኢትዮዽያ ፕሪምየር ቻምፒይና የነበረው እና አሁን ስምንተኛ ሳምንት ባስቆጠረው የ2014: ፕሪሚየር ሊግ በመሪነት ላይ የሚገኘው የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ቡድን ፋሲል ከነማ እስካሁን ባደረጋቸው 7 ጨዋታዎች በ14 ነጥብ የሊጉን መሪነት ይዞ ሲገኝ ሁለተኛ ደረጃ የሚከተለው ባህርዳር ከተማ እና ወላይታ ድቻን በአንድ ነጥብ በልጦ እየመራ ይገኛል።
የሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ ዛሬ በ12 : 00 ሰዓት ከሊጉ ሌላኛው ጠንካራ ተፎካካሪ ከሆነውና በአንድ ነጥብ በሁለተኝነት ከሚከተለው ባህርዳር ከተማ ጋር ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ።
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ የ2013 ዓ.ም ጠንካሬውን ይዞ ዘንድሮም ቻምፒዮና ለመሆን የሚያስችል አቋም እና አቅም አላችሁ ወይ በሚል ዋና አሰልጣኝ ስዩም ከበደን ኢትዮኪክ ጠይቀናቸው አሰልጣኙ ሲመልሱ ” አዎ ። ቡድናችን በጣም ጥሩ አቋም ላይ ነው። በቀጣይ ጨዋታዎችም በዚሁ የሊጉ የመሪነቱን ይዘን እንቀጥላለን”
በማለት ዋና አሰልጣኝ ስዩም ከበደ መልሰዋል ።
በአጥቂ መስመር ፋሲል ከነማ ባለፈው ዓመት የሊጉ ሁለተኛ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ሙጂብ ቃሲም ወደ አልጄሪያ ሊግ መዘዋወሩን ተከትሎ የውድድሩ ጅማሮ ላይ በአጥቂው ቦታ የተለያዩ ሃሳቦች መነሳታቸው ይታወሳል ። ይሁንና በአጥቂ ስፍራ ቡድናችሁ በቋሚነት የሊጉ መሪ ሆኖ የሚያስችል አቅም አላችሁ ወይ ብለን ለጠየቅናቸው ዋና አሰልጣኝ ስዪም ከበደ ቡድናቸው የአጥቂ ስፍራ በቂ የሆነ ጠንካራ አቅም ያላቸው መሆኑንና የዘንድሮው ውድድር መሪ ሆኖ መቀጠል የሚያስችል አቅም እንዳላቸው አረጋግጠውልናል።