ዜናዎች

የሴካፋ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪው ዓሊ ሱሌይማን !

 

በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች እግር ኳስ ፣የኤርትራው ወጣት ዓሊ ሱሌይማን በአራት ጎሎች ቀዳሚውን የጎል አስቆጣሪነት ይመራል ። ተጨዋቾቹ በውደድሩ አራቱንም ጎሎች ያስቆጠረው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ላይ ነው። የመክፈቻ ጨዋታ ላይ ሦስት ጎሎችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል። ዛሬ ደግሞ ቡድኑ ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ከማምራቱ በፊት አንድ ጎሎ  አስቆጥሯል  ።

የኤርትራ ከ23 በታች ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ዓሊ ሱሌይማን በቀጣይ ዓመት በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ሊግ ለመጫወት ከቀናት በፊት በባህርዳር ከነማ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል። በሴካፋ ሻምፒዮናው ላይ የዋልያዎቹ የፊት አጥቂ አቡበከር ናስር በሦስት ጎሎች በሁለተኛነት ደረጃ ላይ ይገኛል።
ዓሊ ሱሌይማን # (  Photo : TIK VAH SPORT )