ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” በርግጠኝነት ሐዋሳ ላይ እንደማገባ አውቅ ነበር ፤ ለአሰልጣኙም ካላገባው ቦርሳዬን ይዤ እንደምሄድ ነበር የነገርኩት ” -አብዲሳ ጀማል

አብዲሳ ጀማል – አዳማ ከተማ

 የአዳማ ከተማው አብዲሳ ጀማል በውድድር ዓመቱ ዘጠኝ ጎሎች አስቆጥሯል። ምንም እንኳ አዳማ ከተማ በቀጣይ አመት ከሊጉ መሰናበቱን ያረጋገጠ ቢሆንም የተጨዋቹ የግል ብቃት አድናቆት የተቸረው ነው። የዛሬውን ጨዋታ ጨምሮ አብዲሳ በውድድር ዓመቱ ካስቆጠራቸው ዘጠኝ ጎሎች አምስቱ በሐዋሳ ከተማ ላይ  የተቆጠሩ ናቹው። ይህን  እና ተጨማሪ ጥያቄዎችን  በተመለከተ  ከጨዋታው በኃላ ከሱፐር ስፓርት ጋር አብዲሳ ጀማል ቆይታ አድርጓል።

ካስቆጠራቸው 9 ጎሎች 5 በሐዋሳ ከተማ ላይ ስለመሆኑ የተለየ ነገር ካለው
” ያው ያጋጥማል። ማለት ተከታታይ ጨዋታዎች ጫና ላይ ነበረን። ከዛ ለመውጣት ብዙ ጥረናል ቡድኑ ገና አዲስ የተዋሀደ ነው።ከአቻ ወደ ማሸነፍ መጥተናል። ጊዜዎች ቢኖሩ ቡድኑን መታደግ እንችል ነበር”
የመጀመሪያው ዙር ላይ ሐዋሳ ላይ ሶስት ጎሎች አስቆጥረህ ነበር ፣ ዛሬም ስትመጣ አገባለሁ ብለህ ነበር ?
” በርግጠኝነት ሐዋሳ ላይ እንደማገባ አውቅ ነበር ፤ ለአሰልጣኙም ጋር ካላገባው ቦርሳዬን ይዤ እንደምሄድ ነበር የነገርኩት (በፈገግታ) እና ተሳክቶልኛል። ደስ ይል ነበረ ጨዋታው”
ቡድናችሁ ከወረደ በኃላ የነፃነት ስሜት ውስጣቸው ስለመኖሩ
“አዎ ትንሽ ነፃነት ይኖረዋል፤ ግን ፤ ያን ያህል አይደለም። ማለት ሙሉ ለሙሉ ወርዷል ብለን አላሰብንም እስካሁን። ችለን ብናተርፈው ደስ ይለናል ። ግን ያው የሆኑ ዕድሎች ስላሉ እሱን ለመጠበቅ ቡድኑን ማዋሀድ አለብን”
ከከፍተኛ ሊግ ክለቦች ጋር በቀጣይ የሚያደርጉትን የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎችን እያሰቡ ሰለመጫወታቸው ?
” አዎ። እያሰብን ነው የምንጫወተው ። ቡድኑ አዲስ ስብስብ ስለሆነ እሱን አስተካክለን ፤ አንደ ጨዋታ ስለምናገኝ እሱን አሸንፈን ወደ ሊጉ ለመመለስ ነው ጥረታችን”
ሁለቱን ጎሎች አበርክት ብትባል ለሚለው
“ለእናቴ  ፤ በአለም ነው ለእሷ ነው የማበረክተው”