ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“በርካታ ጎል የማስቆጠር አጋጣሚዎች አግኝተን ነበር”- ፍራንክ ናፓልን (ቅዱስ ጊዮርጊስ )

የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከሰበታ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ 51% የኳስ ቁጥጥር ነበረው እና 17 ጊዜ ወደ ጎል የሞከረ ሲሆን 6 ጊዜ ሂላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን አድርጓል ። አዲሱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ዋና አሰልጣኝ እንግሊዛዊው ፍራንክ ናፓልን የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያለ ጎል ጀምረዋል። በዛሬው ጨዋታ ከሱፐር ስፖርት ጋር ያደረጉት ቆይታ።
የመጀመሪያው አጋማሽ ያገኟቸው 9 የሚደረሱ ዕድሎች ያለመጠቀቻሁ አበሳጫጭቶታል ?
“እንግዲህ በርካታ ጎል የማስቆጠር አጋጣሚዎች አግኝተን ነበር። እንዳልከው ጎሎችን ለማስቆጠር በርካታ የጎል ዕድሎች እና የማገባት ሙከራዎችን አግኝተን ነበር። ለዚህ ደግሞ በቅድሚያ የተጠቀምነው የቡድን ስራን ጠቅሞንም ነበር ። ካዛ በመነሳት ከምንም በላይ ኳሱን በበላይነት ተቆጣጥሮ ነበር የተጫወትነው። ከዛም በተጨማሪም ጥሪ
ግብ ሙከራዎችን ፈጥረን ነበር ግን ጨዋታውን አጠናቀናል።
ግብ ጠባቂው ባህሩ ነጋሽ በዛሬው ጨዋታ ጫና መሆን እና ካሳየውን ብቃት በመነሳት የጨዋታው ምርጥ ሊባል ይችላል ለሚለው ?
“በርግጥ በጨዋታው ጫና ውስጥ ነው ነበር ፤ግን ደግሞ የጨዋታውን ሙሉ ጊዜ ጫና ውስጥ ወይም በስራ ተጠምዶ አልነበረም። ሆኖም እንደጠበኩት ስራውን በአግባቡ ተወጥቷል ።
የዛሬው ጨዋታ 4-3-3 አሰላለፍ እና የመስመር ተከላካዮች በተመለከተ
እንደጠበኩት በአግባቡ ተወጥተዋል። ሜንሱ በጠበኩት መልኩ ባይሆንም ግን ቦታውን በማስጠበቅ እና በቡድን ስራ ያንን በጥምረት በመተግር ጥሩ ነበር ማለት እችላለሁ። የሚነገረውንም ይተገብርም ነበር።

One thought on ““በርካታ ጎል የማስቆጠር አጋጣሚዎች አግኝተን ነበር”- ፍራንክ ናፓልን (ቅዱስ ጊዮርጊስ )

  1. Betam arife chewata nebar gin dagemo ehie chewata wode gole bikayere best nebar yalefew alefewal leketayûe mazegajete yasefelegale Bunan mashenefe alebene hulegizeme viva sanjeye

Comments are closed.