አትሌቲክስ ዜናዎች

በምድብ 1 : ተወዳዳሪ አትሌት ለሜቻ ግርማ

የዛሬ ሌሊት 3ሺ ሜትር የወንዶች መሠናክል ማጣሪያ ከሌሊቱ 9 :30 ሰዓት ይጀመራል . አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3000 መሰናክ በዶሀ የአለም ሻንፒዮና ላይ የብር ሜዳሊያ ማግኘት የቻለ ወጣት አትሌት ነው። በቅርቡ በሞናኮ ተካሄዶ በነበረው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኬኒያዊያንን አሸንፎ የአመቱን ፈጣን ሰአት አስመዝግቦ ማሸነፉ ይታወሳል።
አትሌቱ በአሁን ሰዓት በርቀቱ ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው አትሌቶች አንዱ ነው። ምንም እንኳ አትሌት ለሜቻ በኢትዮጵያ ሻንፒዮና በህመም ምክንያት ባለመሳተፉ በአትሌቱ ምርጫ ላይ ወዝግብ አስነስቶ ነበር። ፌዴሬሽኑ በአትሌቱ ቦታ አትሌት ሀይለማሪያም አማረን ከተመረጠ በኋላ በቅርቡ በሞናኮ ያሳየው ድንቅ ውጤት እና ወቅታዊ አቋሙ ኦሎምፒክ ኮሚቴው በራሱ በመጨረሻው ምርጫ ማካተቱ ይታወሳል። አትሌት ለሜቻ ግርማ ሌሊት 9:30 በሚያደረገው የ3ሺ መሰናክል ማጣሪያ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል።